Logoja YouVersion
Ikona e kërkimit

ኦሪት ዘፍጥረት 5

5
1የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ 2ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፤ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። 3አዳምም ሁለት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ልጅንም በምሳሌው እንደ መልኩ ወለደ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው። 4አዳምም ሴትን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወስደ። 5አዳምም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ሞተም።
6ሴትም ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖረ፤ 7ሄኖስንም ወለደ፤ ሴትም ሄኖስን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሰባት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። 8ሴትም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥራ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም።
9ሄኖስም መቶ ዘጠና ዓመት ኖረ፤ ቃይናንንም ወለደ፤ 10ሄኖስም ቃይናንን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ አሥራ አምስት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። 11ሄኖስም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አምስት ዓመት ሆነ ሞተም።
12ቃይናንም መቶ ሰባ ዓምት ኖረ፤ 13መላልኤልንም ወለደ፤ ቃይናንም መላልኤልን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። 14ቃይናንም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ አሥር ዓመት ሆነ ሞተም። 15መላልኤልም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ያሬድንም ወለደ። 16መላልኤልም ያሬድን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሠላሳ ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንችም ወለደ። 17መላልኤልም የኖረበት ዘመን ሁሉ ስምንት መቶ ዘጠና አምስት ዓመት ሆነ ሞተም።
18ያሬድም መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ኖረ፤ 19ሄኖክንም ወለደ ያሬድም ሄኖክን ከወለደ በኍላ የኖረው ስምንት መቶ ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። 20ያሬድም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ሁለት ዓመት ሆነ ሞተም። 21ሄኖክም መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ኖረ፤ ማቱሳላንም ወለደ፤ ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፤ 22ማቱሳላንም ከወለደ በኍላ የኖረው ሁለት መቶ ዓመት ሆነ ወለደ። 23ሄኖክም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ። 24ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።
25ማቱሳላም መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ላሜሕንም ወለደ፤ 26ማቱሳላም ላሜሕን ከወለደ በኍላ የኖረው ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ሆነ፤ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። 27ማቱሳላም የኖረበት ዘመን ሁሉ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ ሞትም።
28ላሜሕም መቶ ሰማንያ ሁለት ዓመት ኖረ፤ ልጅንም ወለደ። 29ስሙንም፤ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከተግባራችንና ከእጅ ሥራችን ይህ ያሳርፈናል ሲል ኖኅ ብሎ ጠራው። 30ላሜሕም ኖኅን ከወለደ በኍላ የኖረው አምስት መቶ ስድሳ አምስት ዓመት ሆነ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ። 31ላሜሕ የኖረበት ዘመን ሁሉ ሰባት መቶ አርባ ዓመት ሆነ ሞተም። 32ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ፤ ኖኅም ሴምን ካምን ያፌትንም ወለደ።

Aktualisht i përzgjedhur:

ኦሪት ዘፍጥረት 5: አማ54

Thekso

Ndaje

Copy

None

A doni që theksimet tuaja të jenë të ruajtura në të gjitha pajisjet që keni? Regjistrohu ose hyr