ዘፍጥረት 10
10
የኖኅ ልጆች ትውልድ
1የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ እነርሱም ራሳቸው ከጥፋት ውሃ በኋላ ወንዶች ልጆችን ወለዱ።
የያፌት ዝርያዎች
10፥2-5 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥5-7
2የያፌት ልጆች፦#10፥2 ልጆች ማለት ዘርዐ ትውልዶች ወይም ወራሾች ወይም ሕዝቦች ማለት ሊሆን ይችላል፤ በ3፡4፡6፡7፡20-23፡29 እና 31 እንዲሁ፤
ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕ፣ ቴራስ ናቸው።
3የጋሜር ልጆች፦
አስከናዝ፣ ራፋት፣ ቴርጋማ ናቸው።
4የያዋን ልጆች፦
ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲም፣ ሮዲኢ#10፥4 ጥቂት የማሶሬቲክ የጥንት ጽሑፎች፣ ከኦሪተ ሳምራውያን፣ ሰብዓ ሊቃናትና አብዛኞቹ የማሶሬቲክ የጥናት ጽሑፎች የሚሉት ዶዳኒም ነው። ናቸው። 5ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።
የካም ዝርያዎች
10፥6-20 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥8-16
6የካም ልጆች፦
ኵሽ፣ ምጽራይም፣#10፥6 13ትንም ጨምሮ ግብፅን ያመለክታል። ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው።
7የኵሽ ልጆች፦
ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማ፣ ሰበቅታ ናቸው።
የራዕማ ልጆች፦
ሳባ፣ ድዳን ናቸው።
8ኵሽ የናምሩድ አባት#10፥8 13፡15፡24 እና 26ትን ጨምሮ አባት ማለት ቅድመ አያት ወይም ተተኪ ወይም መሥራች ማለት ሊሆን ይችላል። ነበረ፤ ናምሩድም በምድር ላይ ኀያል ሰው እየሆነ ሄደ። 9በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ብርቱ ዐዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ ዐዳኝ” ይባል ነበር። 10የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በ#10፥10 ወይም ኦሬክና አርካድ፣ ሁሉም ሰናዖር#10፥10 ባቢሎን ነው ምድር ነበሩ። 11ከዚያም ምድር ወደ አሦር ወጥቶ ነነዌን፣ ረሆቦትን፣#10፥11 ወይም ነነዌ ከነከተማዋ አደባባዮች ካለህን 12እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ።
13ምጽራይም፦
የሉዳማውያን፣ የዕሚማውያን፣ ላህቢያውያን፣ የነፍታሌማውያን፣ 14የፈትሩሲማውያን፣ ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የኮስሉሂማውያን፣ የቀፍቶሪማውያን አባት ነበረ።
15ከነዓንም፦
የበኵር ልጁ#10፥15 ወይም ከሲዶናውያን የመጀመሪያው የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣ 16የኢያቡሳውያን፣ የአሞራውያን፣ የጌርሳውያን አባት ነበረ፤ 17እንዲሁም የኤዊያውያን፣ የዑር ኬዋናውያን፣ የሲኒያውያን፣ 18የአራዴዎናውያን፣ የሰማሪናውያን፣ የአማቲያውያን አባት ነበረ።
ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤ 19የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል እስከ ጋዛ ይደርሳል፤ ከዚያም በሰዶም በኩል ገሞራን፣ አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
20እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ናቸው።
የሴም ዝርያዎች
10፥21-31 ተጓ ምብ – ዘፍ 11፥10-27፤ 1ዜና 1፥17-27
21ለያፌት ታላቅ ወንድም#10፥21 ወይም ሴም፣ የ…ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።
22የሴም ልጆች፦
ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።
23የአራም ልጆች፦
ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ#10፥23 ሰብዓ ሊቃናትንና 1ዜና 1፥17 ይመ፤ በዕብራይስጡ ማሽ ይለዋል። ናቸው።
24አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤#10፥24 ከዕብራይስጡ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ሰብዓ ሊቃናት ግን የቃይናን አባት፣ ቃይናንም የ…አባት ነበረ ይላል።
ሳላም ዔቦርን ወለደ።
25ለዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤
አንደኛው ልጅ በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለ ነበር ፍሌቅ#10፥25 ፍሌቅ ማለት ክፍፍል ማለት ነው። ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
26ዮቅጣንም፦
የኤልሞሳድ፣ የሣሌፍ፣ የሐስረሞት፣ የያራሕ፣ 27የሀደራም፣ የአውዛል፣ የደቅላ አባት ነበረ፤ 28እንዲሁም የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣ 29የኦፊር፣ የኤውላጥ፣ የዮባል አባት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው።
30መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል።
31እነዚህም በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው፣ በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ናቸው።
32የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።
Nu markerat:
ዘፍጥረት 10: NASV
Märk
Dela
Kopiera
Vill du ha dina höjdpunkter sparade på alla dina enheter? Registrera dig eller logga in
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጅ መብት © 2001 በ Biblica, Inc.
ፈቃድ የተገኘባቸው ናቸው። መብቱ በመላው ዓለም በሕግ የተጠበቀ።
Holy Bible, New Amharic Standard Version™ (Addisu Medebegna Tirgum™)
Copyright © 2001 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.

: