1
የሉቃስ ወንጌል 8:15
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ግን በመልካምና በቅን ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁትን ነው፤ እነርሱ በቃሉ ጸንተው ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
Linganisha
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:15
2
የሉቃስ ወንጌል 8:14
በእሾኽም ቊጥቋጦ መካከል የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን የዚህ ዓለም ሐሳብና ሀብት፥ የምድራዊ ኑሮ ምቾትም አንቆ ያለ ፍሬ ያስቀራቸዋል።
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:14
3
የሉቃስ ወንጌል 8:13
በጭንጫማ መሬት ላይ የወደቀውም ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ሰምተው በደስታ የሚቀበሉትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የሚያምኑት ለጊዜው ነው፤ ሥር ስለሌላቸውም በፈተና ጊዜ ወዲያውኑ ይክዳሉ።
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:13
4
የሉቃስ ወንጌል 8:25
ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን እጅግ ተደንቀውና ፈርተው እርስ በርሳቸው፥ “ነፋስንና ማዕበልን ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ለመሆኑ ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:25
5
የሉቃስ ወንጌል 8:12
በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ለጊዜው የሚሰሙትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ አምነው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:12
6
የሉቃስ ወንጌል 8:17
“እንዲሁም የተሸሸገ ሳይገለጥ፥ የተሰወረ ሳይታወቅ የሚቀር የለም።
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:17
7
የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
ሴትዮዋም እንዳልተሰወረች ባወቀች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ወደ ኢየሱስ መጥታ በእግሩ ሥር ወደቀች፤ ከዚያም በኋላ ለምን እንደ ነካችውና እንዴት ወዲያውኑ እንደ ተፈወሰችም በሕዝቡ ሁሉ ፊት ገለጠች። ኢየሱስም “ልጄ ሆይ፥ እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ!” አላት።
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:47-48
8
የሉቃስ ወንጌል 8:24
ደቀ መዛሙርቱ “መምህር ሆይ! መምህር ሆይ! ልናልቅ ነው!” ሲሉ ኢየሱስን ቀሰቀሱት። እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የሚያናውጠውን ማዕበል ገሠጻቸው፤ ነፋሱና የሚያናውጠው ማዕበል ወዲያውኑ ቆሙ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
Chunguza የሉቃስ ወንጌል 8:24
Nyumbani
Bibilia
Mipango
Video