ኦሪት ዘፍጥረት 1
1
የፍጥረት ታሪክ
1በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። 2ምድር ግን ባዶ ነበረች፤ አትታይምም#“አትታይም” በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ነበር፤ የተዘጋጀችም አልነበረችም፤ ጨለማም በውኃው ላይ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃው ላይ ይሰፍፍ ነበር። 3እግዚአብሔርም፥ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
4እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ እግዚአብሔርም በብርሃኑና በጨለማው መካከል ለየ። 5እግዚአብሔርም ብርሃኑን “ቀን፥” ጨለማውንም “ሌሊት” ብሎ ጠራው። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ አንደኛ ቀንም ሆነ። 6እግዚአብሔርም፥ “በውኃው መካከል ጠፈር ይሁን፤ በውኃና በውኃ መካከልም ይለይ” አለ፤ እንዲሁም ሆነ።
7እግዚአብሔርም ጠፈርን አደረገ፤ ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትንም ውኆች ለየ። 8እግዚአብሔር ያን ጠፈር “ሰማይ” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ሁለተኛም ቀን ሆነ።
9እግዚአብሔርም ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ከሰማይ በታች ያለው ውኃም በመጠራቀሚያው ተሰበሰበ፤ የብሱም ተገለጠ። 10እግዚአብሔርም የብሱን “ምድር” ብሎ ጠራው፤ የውኃ መጠራቀሚያውንም “ባሕር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። 11እግዚአብሔርም “ምድር በየዘሩ፥#“በየዘሩ” በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በየወገኑና በየመልኩ ዘር የሚሰጥ ቡቃያን፥ በምድርም ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ ታብቅል” አለ፤ እንዲሁም ሆነ። 12ምድርም በየዘሩ፥#“በየዘሩ” በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በየወገኑና በየመልኩ የሚዘራ ቡቃያን፥ በምድር ላይ በየወገኑ ዘሩ በውስጡ የሚገኘውንና ፍሬ የሚያፈራውን ዛፍ አበቀለች። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። 13ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ። ሦስተኛም ቀን ሆነ።
14እግዚአብሔርም አለ፥ “በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀንና በሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች፥ ለዘመናት፥ ለዕለታት፥ ለዓመታትም ይሁኑ። 15በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በሰማይ ጠፈር ለማብራት ይሁኑ፤” እንዲሁም ሆነ። 16እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ፤ ትልቁ ብርሃን ቀንን እንዲመግብ፥ ትንሹ ብርሃንም ከከዋክብት ጋር ሌሊትን እንዲመግብ አደረገ። 17እግዚአብሔርም በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በሰማይ ጠፈር አኖራቸው፤ 18መዓልትንና ሌሊትንም እንዲመግቡ፥ በመዓልትና በሌሊትም መካከል እንዲለዩ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። 19ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ አራተኛም ቀን ሆነ።
20እግዚአብሔርም አለ፥ “ውኃ የሕይወት እስትንፋስ ያላቸውን ተንቀሳቃሾችና በምድር ላይ ከሰማይ በታች የሚበርሩ#ዕብ. “አዕዋፍም ይብረሩ” ይላል። አዕዋፍን ታስገኝ፥” እንዲሁም ሆነ። 21እግዚአብሔርም ታላላቅ አንበሪዎችን፥ ውኃ ያስገኘውን ተንቀሳቃሽ ሕያው ፍጥረትን ሁሉ በየወገኑ፥ የሚበርሩ አዕዋፍንም ሁሉ በየወገናቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ። 22እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ባረካቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙም፤ የባሕርንም ውኃ ሙሉአት፤ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ።” 23ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ አምስተኛም ቀን ሆነ።
24እግዚአብሔርም አለ፥ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደ ወገኑ፥ እንስሳትንና ተንቀሳቃሾችን፥ የምድር አራዊትንም እንደየወገኑ ታውጣ፥” እንዲሁም ሆነ። 25እግዚአብሔርም የምድር አራዊትን እንደየወገኑ፥ እንስሳትንም እንደየወገኑ፥ በምድር የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ እንደየወገኑ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ያ መልካም እንደሆነ አየ።
26እግዚአብሔርም አለ፥ “ሰውን በአርኣያችንና በአምሳላችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥#“አራዊትን” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ።” 27እግዚአብሔርም ሰውን በእግዚአብሔር አምሳል ፈጠረው። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። 28እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥#ዕብ. “እግዚአብሔርም አላቸው” ይላል። “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “አራዊትን” አይጽፍም። የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”
29እግዚአብሔርም አለ፥ “እነሆ፥ መብል ይሆናችሁ ዘንድ በየዘሩ የሚዘራውንና የሚበቅለውን፥ በምድር ሁሉ ላይ የምትዘሩትን የእህል ፍሬ፥ ዘሩ በውስጡ ያለውን ቡቃያ፥ በየፍሬውም የሚዘራውን ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ። 30ለምድር አራዊት ሁሉ፥ ለሰማይም ወፎች ሁሉ፥ ሕያው ነፍስ ላላቸው ለምድር ተንቀሳቃሾችም ሁሉ ሐመልማሉ ሁሉ መብል ይሁንላችሁ።” እንዲሁም ሆነ። 31እግዚአብሔርም የፈጠረውን ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ። ማታም ሆነ፤ ጥዋትም ሆነ፤ ስድስተኛም ቀን ሆነ።
Iliyochaguliwa sasa
ኦሪት ዘፍጥረት 1: አማ2000
Kuonyesha
Shirikisha
Nakili
Je, ungependa vivutio vyako vihifadhiwe kwenye vifaa vyako vyote? Jisajili au ingia

: