ኦሪት ዘፍጥረት 15
15
እግዚአብሔር ለአብራም ቃል ኪዳንን እንደ ሰጠው
1ከዚህም ነገር በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፤ እንዲህ ሲል፥ “አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ፤ ዋጋህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።” 2አብራምም፥ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምን ትሰጠኛለህ? እነሆ፥ ልጅ ሳልወልድ እሞታለሁ፤ የቤቴም ወራሽ ከዘመዴ ወገን የሚሆን የደማስቆ ሰው የማሴቅ ልጅ ይህ ኢያውብር#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ኤሊዔዜር” ይላል። ነው” አለ። 3አብራምም፥ “ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ የዘመዴ ልጅ እርሱ ይወርሰኛል” አለ። 4ያን ጊዜም የአግዚአብሔር ቃል ወደ አብራም እንዲህ ሲል መጣ፤ “እርሱ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚወጣው እርሱ ይወርስሃል።” 5ወደ ሜዳም አወጣውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ ልትቈጥራቸው ትችል እንደሆነ ከዋክብትን ቍጠራቸው። ዘርህም እንደዚሁ ነው” አለው። 6አብራምም በእግዚአብሔር አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። 7“ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው። 8“አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደምወርሳት በምን አውቃለሁ?” አለው። 9እርሱም አለው፥ “የሦስት ዓመት ላም፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም አምጣ፤ እኒህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፤ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው።”#“ይህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፥ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። 10እንዲሁም እነዚህን ሁሉ ወሰደለት፤ በየሁለትም ከፈላቸው፤ የተከፈሉትንም በየወገኑ ትይዩ አደረጋቸው፤ ወፎችን ግን አልቈረጣቸውም። 11አሞራዎችም በተቈረጠው ሥጋቸው ላይ ወረዱ፤ አብራምም በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ አባረራቸው።
12ፀሐይም በገባ ጊዜ በአብራም ድንጋጤ#ዕብ. “ከባድ ዕንቅልፍ” ይላል። መጣበት፤ እነሆም፥ የሚያስፈራ ጽኑዕ ጨለማ መጣበት፤ 13እግዚአብሔርም አብራምን አለው፥ “ዘርህ ለእነርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመታትም ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል፤ ያሠቃዩአቸዋል፤ ያስጨንቋቸዋልም። 14ደግሞም የሚያሠቃዩአቸውን እኔ እፈርድባቸዋለሁ። ከዚህም በኋላ ከብዙ ገንዘብ ጋር ወደዚህ ይወጣሉ። 15አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፤ በመልካም ሽምግልናም ትቀበራለህ። 16በአራተኛው ትውልድ ግን ወደዚህ ይመለሳሉ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የአሞራውያን ኀጢአት አልተፈጸመምና።” 17እንዲህም ሆነ፤ ፀሐይም በገባ ጊዜ ነበልባል መጣ፤ የእሳት መብራትና የሚጤስ ምድጃም መጣ፤ በዚያም በተከፈለው መካከል አለፈ። 18በዚያችም ቀን እግዚአብሔር ለአብራም ተስፋ ያደረገለትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እንዲህም አለው፥ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣታለሁ፤ 19ቀኔዎሳውያንን፥ ቄኔዜዎሳውያንን፥ ቄኔሚሎሳውያንን፥ 20ኬጤዎናውያንንም፥ ፌርዜዎናውያንንም፥ ፈራዮናውያንንም፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ራፋይምን” ይላል። 21አሞሬዎናውያንንም፥ ከናኔዎናውያንንም፥ ጌርጌሴዎናውያንንም፥#በግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤዌዎናውያን” የሚል አለ። ኢያቡሴዎናውያንንም።”
Поточний вибір:
ኦሪት ዘፍጥረት 15: አማ2000
Позначайте
Поділитись
Копіювати
Хочете, щоб ваші позначення зберігалися на всіх ваших пристроях? Зареєструйтеся або увійдіть

: