ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 24

24
የይ​ስ​ሐ​ቅና ርብቃ ጋብቻ
1አብ​ር​ሃ​ምም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን በሁሉ ባረ​ከው። 2አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ውን፥ የቤ​ቱን ሽማ​ግሌ፥ የከ​ብ​ቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦ 3“እጅ​ህን በእጄ ላይ አድ​ርግ፤ እኔም አብሬ ከም​ኖ​ራ​ቸው ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይ​ስ​ሐቅ ሚስት እን​ዳ​ት​ወ​ስ​ድ​ለት በሰ​ማ​ይና በም​ድር አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ል​ሃ​ለሁ፤ 4ነገር ግን ወደ ተወ​ለ​ድ​ሁ​በት ወደ ሀገ​ሬና ወደ ተወ​ላ​ጆች ሂድ፤ ለልጄ ለይ​ስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሚስ​ትን አም​ጣ​ለት።” 5ሎሌ​ውም፥ “ሴቲቱ ምና​ል​ባት ወደ​ዚህ ሀገር ከእኔ ጋር ለመ​ም​ጣት ባት​ወ​ድ​ድስ ልጅ​ህን ወደ መጣ​ህ​በት ሀገር ልመ​ል​ሰ​ውን?” አለው። 6አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “ልጄን ወደ​ዚያ እን​ዳ​ት​መ​ልስ ተጠ​ን​ቀቅ፤ 7ከአ​ባቴ ቤት፥ ከተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባት ምድር ያወ​ጣኝ፦ ‘ይህ​ች​ንም ምድር ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ’ ብሎ የነ​ገ​ረ​ኝና የማ​ለ​ልኝ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እርሱ መል​አ​ኩን በፊ​ትህ ይሰ​ድ​ዳል፤ ከዚ​ያም ለልጄ ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ። 8ሴቲ​ቱም ከአ​ንተ ጋር ወደ​ዚች ምድር ለመ​ም​ጣት ባት​ፈ​ቅድ አንተ ከዚህ መሐላ ንጹሕ ነህ፤ ልጄን ግን ወደ​ዚያ እን​ዳ​ት​መ​ል​ሰው ተጠ​ን​ቀቅ።” 9ሎሌ​ውም በጌ​ታው በአ​ብ​ር​ሃም እጅ ላይ እጁን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ሁም ነገር ማለ​ለት።
10ሎሌ​ውም ከጌ​ታው ግመ​ሎች መካ​ከል ዐሥር ግመ​ሎ​ችን ወስዶ፥ ከጌ​ታ​ውም ዕቃ መል​ካም መል​ካ​ሙን ይዞ ተነሣ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሦርያ ወን​ዞች መካ​ከል#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “መስ​ጴ​ጦ​ምያ” ይላል። ወደ ናኮር ከተማ ሄደ። 11ሲመ​ሽም ውኃ ቀጂ​ዎች ውኃ ሊቀዱ በሚ​መ​ጡ​በት ጊዜ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ውጪ በውኃ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ግመ​ሎ​ቹን አሳ​ረፈ። 12እን​ዲ​ህም አለ፥ “የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤#“እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። መን​ገ​ዴን ዛሬ በፊቴ አቅ​ና​ልኝ፤ ለጌ​ታ​ዬም ለአ​ብ​ር​ሃም ምሕ​ረ​ትን አድ​ርግ። 13እነሆ፥ በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ቆሜ​አ​ለሁ፤ የከ​ተ​ማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆ​ችም ውኃ​ውን ሊቀዱ ይወ​ጣሉ፤ 14እን​ስ​ራ​ሽን አዘ​ን​ብ​ለሽ ውኃ አጠ​ጭኝ የም​ላት እር​ስ​ዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመ​ሎ​ች​ህን ደግሞ እስ​ኪ​ረኩ አጠ​ጣ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እር​ስዋ ለባ​ሪ​ያህ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጀ​ሃት ትሁን፤ በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ለአ​ብ​ር​ሃም ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።” 15እን​ደ​ዚህ በልቡ ያሰ​በ​ውን መና​ገ​ሩን ሳይ​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፦ የአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም የና​ኮር ሚስት የሚ​ልካ ልጅ የባ​ቱ​ኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም በጫ​ን​ቃዋ ተሸ​ክማ ነበር። 16ብላ​ቴ​ና​ይ​ቱም መል​ክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማ​ታ​ውቅ ድን​ግል ነበ​ረች። ወደ ውኃው ጕድ​ጓ​ድም ወረ​ደች፤ ውኃም ቀዳች፤ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም ሞልታ ወጣች። 17ያም ሰው ሊገ​ና​ኛት ሮጠና፥ “ከእ​ን​ስ​ራሽ ጥቂት ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት። 18እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ጠጣ” አለ​ችው፤ ፈጥ​ናም እን​ስ​ራ​ዋን ከጫ​ን​ቃዋ በእ​ጅዋ አው​ርዳ እስ​ኪ​ረካ አጠ​ጣ​ችው። 19እር​ሱ​ንም ከአ​ጠ​ጣች በኋላ፦#“እር​ሱ​ንም ካጠ​ጣች በኋላ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ ነው። “ለግ​መ​ሎ​ችህ ደግሞ ሁሉም እስ​ኪ​ረኩ ድረስ ውኃ እቀ​ዳ​ለሁ” አለ​ችው። 20ፈጥ​ናም ውኃ​ውን ከእ​ን​ስ​ራዋ በማ​ጠ​ጫው ውስጥ ገለ​በ​ጠ​ችው፤ ደግ​ሞም ልት​ቀዳ ወደ ጕድ​ጓዱ ሮጠች፤ ለግ​መ​ሎ​ቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች። 21ሰው​የ​ውም ትክ ብሎ ይመ​ለ​ከ​ታት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዱን አቅ​ን​ቶ​ለት እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ ለማ​ወ​ቅም ዝም አለ። 22ግመ​ሎ​ቹም ከጠጡ በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ ሰው​ዬው አንድ አንድ ወቄት የሚ​መ​ዝን የወ​ርቅ ጉትቻ፥ ለእ​ጆ​ች​ዋም ዐሥር ወቄት የሚ​መ​ዝን ጥንድ የወ​ርቅ አም​ባር አወጣ፤ 23ጠር​ቶም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? በአ​ባ​ትሽ ቤት የም​ና​ድ​ር​በት ስፍራ እን​ዳለ እስኪ ንገ​ሪኝ፤” 24አለ​ች​ውም፥ “እኔ ሚልካ ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት የባ​ቱ​ኤል ልጅ ነኝ። 25በእኛ ዘንድ ለግ​መ​ሎ​ችህ ሣርና ገለባ የሚ​በቃ ያህል አለ፤ ማደ​ሪ​ያም አለን።” 26ሰው​የ​ውም ደስ አለው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰገደ። 27እን​ዲ​ህም አለ፥ “ቸር​ነ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ከጌ​ታዬ ያላ​ራቀ የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ ለእ​ኔም ወደ ጌታዬ ወደ አብ​ር​ሃም ወን​ድም ቤት መን​ገ​ዴን አቀ​ና​ልኝ።”
28ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም ሮጠች፥ ለእ​ና​ቷም ቤት ይህን ሁሉ ነገር ተና​ገ​ረች። 29ለር​ብ​ቃም ስሙ ላባ የተ​ባለ ወን​ድም ነበ​ራት፤ ላባም ወደ ውጪ ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ ወደ ሰው​ዬው ሮጠ። 30ጉት​ቻ​ው​ንና አም​ባ​ሮ​ቹን በእ​ኅቱ እጅ ባየ ጊዜ፥ የእ​ኅ​ቱ​ንም የር​ብ​ቃን ነገር፦ ያ ሰው እን​ዲህ አለኝ ያለ​ች​ውን በሰማ ጊዜ፥ እርሱ ወደ​ዚያ ሰው መጣ፤ እነ​ሆም በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ከግ​መ​ሎቹ ዘንድ ቆሞ ነበር። 31እር​ሱም አለው፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ፥ ግባ ስለ​ምን አንተ በውጪ ቆመ​ሃል? እኛም ቤትን፥ ለግ​መ​ሎ​ች​ህም ማደ​ሪ​ያን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ናል።”#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “እኔም ቤቱን፥ ለግ​መ​ሎ​ች​ህም ገፈ​ራን አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ” ይላል። 32ሰው​ዬ​ውም ወደ ቤት ገባ፤ ግመ​ሎ​ቹ​ንም አራ​ገፈ፤ ለግ​መ​ሎ​ቹም ሣርና ገለባ አቀ​ረ​ቡ​ላ​ቸው፤ እግ​ሩን ይታ​ጠብ ዘንድ ውኃ አመ​ጡ​ለት፤ ከእ​ርሱ ጋር ላሉ ሰዎ​ችም አመ​ጡ​ላ​ቸው። 33ይበ​ላም ዘንድ እን​ጀ​ራን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ እርሱ ግን “ነገ​ሬን እስ​ክ​ና​ገር ደረስ አል​በ​ላም” አለ። እነ​ር​ሱም “ተና​ገር” አሉት። 34እር​ሱም አለ፥ “እኔ የአ​ብ​ር​ሃም ሎሌ ነኝ። 35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌታ​ዬን እጅግ ባረ​ከው፤ አገ​ነ​ነ​ውም፤ ላሞ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ወን​ዶች ባሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ግመ​ሎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም ሰጠው። 36የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም ሚስት ሣራም በእ​ር​ጅ​ናዋ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በእ​ር​ጅ​ናው” ይላል። ለጌ​ታዬ ወንድ ልጅን ወለ​ደች፤ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሁሉ ሰጠው።” 37ጌታዬ እን​ዲህ ሲል አማ​ለኝ፥ “እኔ ካለ​ሁ​በት ሀገር ከከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ሴቶች ልጆች ለልጄ ሚስ​ትን አት​ው​ሰድ፤ 38ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገ​ኔም ሂድ፤ ለል​ጄም ከዚያ ሚስ​ትን ውሰ​ድ​ለት። 39ጌታ​ዬ​ንም ሴቲቱ ምና​ል​ባት ከእኔ ጋር መም​ጣ​ትን ባት​ፈ​ቅ​ድስ አል​ሁት። 40እር​ሱም አለኝ፦ አካ​ሄ​ዴን በፊቱ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ከአ​ንተ ጋር ይል​ካል። መን​ገ​ድ​ህ​ንም ያቀ​ናል፤ ለል​ጄም ከወ​ገ​ኖች ከአ​ባ​ቴም ቤት ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ 41የዚ​ያን ጊዜ ከመ​ሐ​ላዬ ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ፤ ወደ ዘመ​ዶች ሄደህ እነ​ርሱ ባይ​ሰ​ጡህ ካማ​ል​ሁህ መሐላ ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ።” 42ዛሬም ወደ ውኃው ጕድ​ጓድ መጣሁ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ዛሬ የም​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ዴን ብታ​ቀ​ና​ልኝ፥ 43እነሆ፥ እኔ በው​ኃው ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ቆሜ​አ​ለሁ፤ የከ​ተ​ማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆ​ችም ውኃን ሊቀዱ ይወ​ጣሉ፤ ጥቂት ውኃ ከእ​ን​ስ​ራሽ አጠ​ጪኝ ስላት፥ 44እር​ስ​ዋም ፦ ‘አንተ ጠጣ፤ ደግ​ሞም ለግ​መ​ሎ​ችህ እቀ​ዳ​ለሁ’ የም​ት​ለኝ ድን​ግል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ ልጅ ለባ​ሪ​ያዉ ለይ​ስ​ሐቅ ያዘ​ጋ​ጃት ሚስት እር​ስዋ ትሁን። በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ።”#“በዚ​ህም ለጌ​ታዬ ምሕ​ረ​ትን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ አው​ቃ​ለሁ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 45እኔም በልቤ ያሰ​ብ​ሁ​ትን ሳል​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፤ ያን ጊዜ ርብቃ እን​ስ​ራ​ዋን በት​ከ​ሻዋ ተሸ​ክማ ወጣች፥ ወደ ምን​ጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች፤ እኔም “እስቲ ውኃ አጠ​ጪኝ” አል​ኋት። 46ፈጥ​ናም እን​ስ​ራ​ዋን ከት​ከ​ሻዋ አወ​ረ​ደ​ችና፥ “አንተ ጠጣ፤ ግመ​ሎ​ች​ህን ደግሞ አጠ​ጣ​ለሁ” አለ​ችኝ፤ እኔም ጠጣሁ፤ ግመ​ሎ​ች​ንም ደግሞ አጠ​ጣች። 47እኔም “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? ንገ​ሪኝ” ብዬ ጠየ​ቅ​ኋት። እር​ስ​ዋም፥ “ሚልካ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የና​ኮር ልጅ የባ​ቱ​ኤል ልጅ ነኝ” አለ​ችኝ፤ 48ይህ​ንም ነገር ከአ​ን​ደ​በቷ በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ።#“ይህ​ንም ነገር ከአ​ን​ደ​በቷ በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። ለጆ​ሮ​ዎ​ች​ዋም ጉት​ቻ​ዎ​ችን ለእ​ጆ​ች​ዋም አም​ባ​ሮ​ችን አድ​ርጌ አስ​ጌ​ጥ​ኋት። ደስ ባሰ​ኘ​ች​ኝም ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገ​ድሁ፤ የጌ​ታ​ዬን የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ለልጁ እወ​ስድ ዘንድ በቀና መን​ገድ የመ​ራ​ኝን የጌ​ታ​ዬን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ንሁ። 49አሁ​ንም ቸር​ነ​ት​ንና እው​ነ​ትን ለጌ​ታዬ ትሠሩ እንደ ሆነ ንገ​ሩኝ፤ ይህም ባይ​ሆን ንገ​ሩኝ፤ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ እመ​ለስ ዘንድ። 50ባቱ​ኤ​ልና ላባም መለሱ፤ እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ነገሩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጥ​ቶ​አል፤ ክፉ ወይም በጎ ልን​መ​ል​ስ​ልህ አን​ች​ልም። 51ርብቃ እን​ኋት፤ በፊ​ትህ ናት፤ ይዘ​ሃት ሂድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ለጌ​ታህ ልጅ ሚስት ትሁን።” 52የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ ነገ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ። 53ሎሌ​ውም የብ​ርና የወ​ርቅ ጌጥ፥ ልብ​ስም አወጣ፤ ለር​ብ​ቃም ሰጣት፤ ዳግ​መ​ኛም ለአ​ባ​ቷና ለእ​ናቷ#ዕብ. “ወን​ድ​ምዋ እና እናቷ” ይላል። እጅ መንሻ ሰጣ​ቸው። 54ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ፤ በማ​ለ​ዳም ተነ​ሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው። 55አባቷ እና​ቷና ወን​ድ​ምዋ፦#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ወን​ድ​ሞ​ች​ዋና እናቷ” ይላል ዕብ. “ወን​ድ​ም​ዋና እናቷ” ይላል። “ብላ​ቴ​ና​ዪቱ ዐሥር ቀን ያህል እንኳ በእኛ ዘንድ ትቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም በኋላ ትሄ​ዳ​ለች” አሉ። 56እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዴን አቅ​ን​ቶ​ልኝ ሳለ አታ​ዘ​ግ​ዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው። 57እነ​ር​ሱም፥ “ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን እን​ጥ​ራና ከአ​ፍዋ እን​ጠ​ይቅ” አሉ። 58ርብ​ቃ​ንም ጠር​ተው፥ “ከዚህ ሰው ጋር ትሄ​ጃ​ለ​ሽን?” አሉ​አት። እር​ስ​ዋም፥ “አዎን እሄ​ዳ​ለሁ” አለች። 59እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ርብ​ቃን ሞግ​ዚ​ቷ​ንም#“ሞግ​ዚ​ቷ​ንም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ከገ​ን​ዘብ ጋር፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሎሌና ሰዎ​ቹ​ንም አሰ​ና​በ​ቱ​አ​ቸው። 60እኅ​ታ​ቸው ርብ​ቃ​ንም መረ​ቁ​አ​ትና፥ “አንቺ እኅ​ታ​ችን፥ እልፍ አእ​ላ​ፋት ሁኚ፤ ዘር​ሽም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይው​ረስ” አሉ​አት።
61ርብ​ቃም ተነ​ሣች፤ ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ዋም፥ በግ​መ​ሎ​ችዋ ላይ ተቀ​ም​ጠው ከሰ​ው​ዬው ጋር አብ​ረው ሄዱ፤ ሎሌ​ውም ርብ​ቃን ተቀ​ብሎ ሄደ። 62ይስ​ሐ​ቅም በዐ​ዘ​ቅተ ራእይ በኩል ወደ ምድረ በዳ ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በአ​ዜብ በኩል ባለው ምድር ተቀ​ምጦ ነበ​ርና። 63ይስ​ሐ​ቅም በመሸ ጊዜ በልቡ እያ​ሰ​ላ​ሰለ ወደ ሜዳ ወጥቶ ነበር፤ ዓይ​ኖ​ቹ​ንም አቀና፤ እነ​ሆም ግመ​ሎች ሲመጡ አየ። 64ርብ​ቃም ዓይ​ኖ​ች​ዋን አቀ​ናች፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም አየች፤ ከግ​መ​ልም ወረ​ደች። 65ሎሌ​ው​ንም፥ “ሊቀ​በ​ለን በሜዳ የሚ​መጣ ይህ ሰው ማነው?” አለ​ችው። ሎሌ​ውም፥ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፤ እር​ስ​ዋም ቀጸ​ላ​ዋን ወስዳ ተከ​ና​ነ​በች። 66ሎሌ​ውም ያደ​ረ​ገ​ውን ነገር ሁሉ ለይ​ስ​ሐቅ ነገ​ረው። 67ይስ​ሐ​ቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብ​ቃ​ንም ወሰ​ዳት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወደ​ዳት፤ ይስ​ሐ​ቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽ​ናና።

Позначайте

Поділитись

Копіювати

None

Хочете, щоб ваші позначення зберігалися на всіх ваших пристроях? Зареєструйтеся або увійдіть