ኦሪት ዘፍጥረት 11
11
1ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። 2ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ በዚያም ተቀመጡ። 3እርስ በርሳቸውም፤ ኑ ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኩስው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፍት እንደ ጭቃ ሆነችላችው። 4እንዲህም፤ ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስምችንን እናስጠራው አሉ። 5እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። 6እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ እነርሱ አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። 7ኑ፥ እንውረድ፤ እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚይ እንደባልቀው። 8እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው። 9ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፥ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
10የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኍላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ። 11ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኍላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።
12አርፋክስድም መቶ ሠላሳ አምስት ዓመት ኖረ፥ 13ቃይንምንም ወለደ፤ አርፋክስድም ቃይንምንም ከወለደ በኍላ አራት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችም ወለደ፥ ሞተም። ቃይንምም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም ሴቶቸም ወለደ፤ ሞተም።
14ሳላም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ዔቦርንም ወለደ፤ 15ሳላም ዔቦርን ከወለደ በኍላ ሦስት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።
16ዔበርም መቶ ሠላሳ አራት ዓመት ኖረ፥ 17ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔበርም ፋሌቅን ከወለደ በኍላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።
18ፋሌቅም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ 19ራግውንም ወለደ፤ ራግውንም ከወለደ በኍላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችን፥ ሴቶችንም ወለደ ሞተም። 20ራግውም መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመት ኖረ፥ 21ሴሮሕንም ወለደ፤ ራግውም ሴሮሕን ከወለደ በኍላ ሁለት መቶ ሰባት ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም።
22ሴሮሕም መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ 23ናኮርንም ወለደ፤ ናኮርንም ከወለደ በኍላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። 24ናኮርም መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፥ 25ታራንም ወለደ፤ ታራንም ከወለደ በኍላ ናኮር መቶ ሃያ ዘጠኝ ዓመት ኖረ ወንዶችን ሴቶችንም ወለደ ሞተም። 26ታራም መቶ ዓመት ኖረ፥ አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ። 27የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራም አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ። 28ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። 29አብራምና ናኮርም ሚስቶችን አገቡ፤ የአብራም ሚስት ስምዋ ሦራ ነው፤ የናኮር ሚስት የሐራን ልጅ ሚልካ ናት፤ ሐራንም የሚልካና የዩስካ አባት ነው። 30ሦራም መካን ነበረች፤ ልጅ አልነበራትም። 31ታራም ልጁን አብራምንና የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥን የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፤ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ። 32የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካራን ሞተ።
Đang chọn:
ኦሪት ዘፍጥረት 11: አማ54
Tô màu
Chia sẻ
Sao chép
Bạn muốn lưu những tô màu trên tất cả các thiết bị của mình? Đăng ký hoặc đăng nhập

: