የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ
ያዳምጡ ትንቢተ ዮናስ መግቢያ ትንቢተ ዮናስ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልፈጽምም ባለ በአንድ ነቢይ ላይ የሚደርስበትን ልዩ ልዩ ችግር የሚገልጥ የታሪክ መጽሐፍ በመሆኑ ከሌሎች የትንቢት መጻሕፍት የተለየ መልክ አለው። እግዚአብሔር ዮናስን “የእስራኤል ብርቱ ጠላትና የታላቁ የአሦር ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ዋና ከተማ ወደነበረችው ወደ ነነዌ ሂድ!” በማለት አዘዘው፤ ዮናስ ግን “እግዚአብሔር ከተማይቱን ለማጥፋት የሰጠውን ብርቱ ማስጠንቀቂያ በሥራ ላይ አያውለውም” ብሎ ስላሰበ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ይዞ ወደ ነነዌ መሄድ አልፈለገም፥ ብዙ ትርኢታዊ ድርጊቶች ከተፈጸሙ በኋላ ደስ ሳይለው ታዘዘ፥ የጥፋት ትንቢቱም ተፈጻሚነት ሳያገኝ በመቅረቱ አኰረፈ። መጽሐፉ እግዚአብሔር በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለው ያስረዳል፤ ይልቁንም እግዚአብሔር የፍቅርና የምሕረት አምላክ በመሆኑ የሕዝቡን ጠላቶች ከሚቀጣና ከሚደመስስ ይልቅ ይቅር ሊላቸውና ሊያድናቸው እንደሚወድ ያስረዳል።
የመጽሐፍ ቅዱስ መተግበሪያው እንዲያነብልዎ ይፍቀዱ
በየትኛውም ቦታ ቢሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል ያዳምጡ!