1
ዘፍጥረት 24:12
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ከዚያም እንዲህ ሲል ጸለየ፣ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በዛሬው ቀን ጕዳዬን አሳካልኝ፤ ለጌታዬ ለአብርሃም ቸርነትህን አሳየው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ዘፍጥረት 24:14
እንግዲህ፣ ‘እንስራሽን አውርጂና ውሃ አጠጪኝ’ ስላት፣ ‘ዕንካ ጠጣ፤ ግመሎችህንም ላጠጣልህ’ የምትለኝ ቈንጆ እርሷ ለባሪያህ ለይሥሐቅ የመረጥሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ቸርነትህን እንዳሳየኸው ዐውቃለሁ።”
3
ዘፍጥረት 24:67
ይሥሐቅም ርብቃን ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን ይዟት ገባ፤ አገባት፣ ሚስትም ሆነችው፤ እርሱም ወደዳት። ይሥሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና።
4
ዘፍጥረት 24:60
ርብቃንም እንዲህ ብለው መረቋት፤ “እኅታችን ሆይ፤ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽ የጠላቶቹን ደጆች ይውረስ”።
5
ዘፍጥረት 24:3-4
ልጄን፣ በመካከላቸው ከምኖር ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች ጋራ እንዳታጋባው በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ማልልኝ። ነገር ግን ወደ አገሬ፣ ወደ ገዛ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ለይሥሐቅ ሚስት ትፈልግለታለህ።”
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች