1
ዘፍጥረት 46:3
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የአባትህ አምላክ ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ዘፍጥረት 46:4
ዐብሬህ ወደ ግብጽ እወርዳለሁ፤ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፤ የዮሴፍ የራሱ እጆችም ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል።”
3
ዘፍጥረት 46:29
ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደ ደረሰ፣ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረዥም ጊዜ አለቀሰ።
4
ዘፍጥረት 46:30
እስራኤልም ዮሴፍን፣ “በሕይወት መኖርህን ስላየሁ፣ ከእንግዲህ ብሞትም አይቈጨኝ” አለው።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች