1
ማርቆስ 6:31
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ብዙ ሰዎች ይመጡና ይሄዱ ስለ ነበር ምግብ እንኳ ለመብላት ጊዜ ስላልነበራቸው፣ “እስኪ ብቻችሁን ከእኔ ጋራ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ እንሂድና ጥቂት ዕረፉ” አላቸው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ማርቆስ 6:4
ኢየሱስም፣ “ነቢይ የማይከበረው በገዛ አገሩ፣ በዘመዶቹ መካከልና በራሱ ቤት ብቻ ነው” አላቸው።
3
ማርቆስ 6:34
ኢየሱስ ከጀልባዋ በሚወርድበት ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ አየ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩም ዐዘነላቸው፤ ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር።
4
ማርቆስ 6:5-6
እዚያም በጥቂት ሕመምተኞች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወሱ በቀር ምንም ታምራት ሊሠራ አልቻለም፤ ባለማመናቸውም ተደነቀ። ከዚያም ኢየሱስ በየመንደሩ እየተዘዋወረ ያስተምር ነበር።
5
ማርቆስ 6:41-43
እርሱም ዐምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ በማየት ባረከ፤ እንጀራውንም ቈርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ሁለቱንም ዓሣ ለሁሉም አካፈለ። ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከተበላው እንጀራና ዓሣ፣ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ፍርፋሪ አነሡ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች