በመጨረሻዎቹ ቀኖች የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ ዕወቅ፤ ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፥ ትምክሕተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ ውለታቢሶች፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ይቅርታ የማያደርጉ፥ የሰው ስም የሚያጠፉ፥ ራሳቸውን የማይቈጣጠሩ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን ነገር የሚጠሉ፥ ከዳተኞች፥ ጥንቃቄ የሌላቸው፥ በትዕቢት የተነፉ፥ እግዚአብሔርን ከመውደድ ይልቅ ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ ይሆናሉ። እግዚአብሔርን የሚያመልኩ መስለው ይታያሉ፤ የአምልኮትን ኀይል ግን ይክዳሉ፤ እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ራቅ።