1
ኦሪት ዘዳግም 1:30-31
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
በዓይናችሁ እያያችሁ በግብጽ እንዳደረገላችሁ ለእናንተ የሚዋጋው በፊታችሁ የሚሄደው አምላካችሁ እግዚአብሔር ነው። እናንተ ወደዚህ ቦታ እስክትመጡ ድረስ አንድ ሰው ልጁን እንደሚንከባከብ በሄዳችሁበት መንገድ ሁሉ አምላካችሁ እግዚአብሔር በምድረ በዳው እንደ ተንከባከባችሁ አይታችኋል።’
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘዳግም 1:11
አሁንም የቀድሞ አባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ሺህ ጊዜ እጥፍ በመጨመር ቊጥራችሁን አብዝቶ ያበልጽጋችሁ!
3
ኦሪት ዘዳግም 1:6
“በሲና ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን እንዲህ አለን፦ ‘እነሆ፦ በዚህ ተራራ ላይ ለረጅም ጊዜ ቈይታችኋል፤
4
ኦሪት ዘዳግም 1:8
እነሆ፥ ምድሪቱ በፊታችሁ ናት፤ እኔ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ላወርሳቸው የተስፋ ቃል የገባሁላቸውን ምድር ሄዳችሁ ውረሱ።’ ”
5
ኦሪት ዘዳግም 1:17
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’
Home
Bible
Plans
Videos