1
ኦሪት ዘጸአት 34:6-7
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔር በፊቱ ሲያልፍ እንዲህ ብሎ ዐወጀ፤ “እኔ እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሐሪ አምላክ ነኝ፤ እኔ ለቊጣ የዘገየሁ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅሬና ታማኝነቴ የበዛ ነው፤ ዘለዓለማዊ ፍቅሬንም እስከ ብዙ ሺህ ትውልድ እጠብቃለሁ፤ በደልን መተላለፍንና ኃጢአትን ሁሉ ይቅር እላለሁ፤ ነገር ግን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት ከመቅጣት አልገታም።”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘጸአት 34:14
“እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ ከእኔ በቀር ለሌሎች አማልክት አትስገዱ፤
3
ኦሪት ዘጸአት 34:10
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ በፊት በምድር ላይ በማንኛውም ሕዝብ ዘንድ ሆኖ የማያውቅ ድንቅ ነገር በሕዝብህ ፊት አደርጋለሁ፤ አስፈሪ የሆነ ድንቅ ነገር ስለማደርግ እኔ እግዚአብሔር የማደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝቦች ሁሉ ያያሉ።
Home
Bible
Plans
Videos