1
መጽሐፈ መሳፍንት 7:2
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
እግዚአብሔርም ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “በምድያማውያን ላይ ድልን አቀዳጃቸው ዘንድ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች ለእኔ እጅግ ብዙ ሆነዋል፤ በራሳቸው ኀይል የሚያሸንፉ ስለሚመስላቸው ለእኔ ክብር ከመስጠት ይቈጠባሉ፤
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ መሳፍንት 7:7
እግዚአብሔር ጌዴዎንን “በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ በጠጡት በእነዚህ ሦስት መቶ ሰዎች አማካይነት አድናችኋለሁ፤ በምድያማውያን ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርግሃለሁ፤ ለቀሩት ግን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ንገራቸው” አለው።
3
መጽሐፈ መሳፍንት 7:3
ስለዚህ ለሕዝቡ ‘ከመካከላችሁ ፈሪና ድንጉጥ የሆነ ሰው ካለ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፤ እኛም በዚህ በገለዓድ ተራራ ላይ እንቈያለን’ ብለህ ንገራቸው።” በዚህ ምክንያት ኻያ ሁለቱ ሺህ ሲመለሱ ዐሥሩ ሺህ ቀሩ።
4
መጽሐፈ መሳፍንት 7:4
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ጌዴዎንን እንዲህ አለው፦ “አሁንም ገና ብዙ ሠራዊት አሉህ፤ እነርሱን ወደ ወንዝ ውሰዳቸውና በዚያ እኔ እፈትናቸዋለሁ፤ ከአንተ ጋር ይሂድ የምለው ሰው ይሂድ፤ ይቅር የምለው ሰው ደግሞ ይመለስ።”
5
መጽሐፈ መሳፍንት 7:5-6
ጌዴዎንም ሰዎቹን ወደ ወንዝ ውሃ አወረዳቸው፤ እግዚአብሔርም “በጒልበቱ ተንበርክኮ ውሃ ከሚጠጣው መካከል እንደ ውሻ በምላሱ እየጨለፈ የሚጠጣውን ሁሉ ለየው!” አለው። በእጃቸው ውሃ እየዘገኑ የሚጠጡት ቊጥር ሦስት መቶ ሆነ፤ የቀሩት ሁሉ የጠጡት ግን በጒልበታቸው ተንበርክከው ነበር።
Home
Bible
Plans
Videos