1
የሉቃስ ወንጌል 12:40
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
የሰው ልጅም ባላሰባችሁበት ሰዓት በድንገት ይመጣል፤ ስለዚህ እናንተም ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ።”
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የሉቃስ ወንጌል 12:31
ይልቅስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ፈልጉ፤ እነዚህም ነገሮች ሁሉ ይጨመሩላችኋል።
3
የሉቃስ ወንጌል 12:15
ቀጥሎ ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ “የሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት አይደለም፤ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስስትም ተጠበቁ።”
4
የሉቃስ ወንጌል 12:34
ገንዘባችሁ ባለበት ቦታ ልባችሁም በዚያው ይሆናል።”
5
የሉቃስ ወንጌል 12:25
ለመሆኑ ከእናንተ መካከል በመጨነቅ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ማን ነው?
6
የሉቃስ ወንጌል 12:22
ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ “ስለዚህ ለሕወታችሁ ‘ምን እንበላለን? ለሰውነታችሁም ምን እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ እላችኋለሁ።
7
የሉቃስ ወንጌል 12:7
የእናንተማ የራሳችሁ ጠጒር እንኳ በሙሉ የተቈጠረ ነው፤ ስለዚህ አትፍሩ! እናንተ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ።”
8
የሉቃስ ወንጌል 12:32
“እናንተ እንደ ታናናሽ መንጋ የሆናችሁ ወገኖቼ አትፍሩ፤ የሰማይ አባታችሁ መንግሥትን ሊሰጣችሁ ፈቅዶአል።
9
የሉቃስ ወንጌል 12:24
እስቲ ቊራዎችን ተመልከቱ! እነርሱ አይዘሩም ወይም አያጭዱም፤ የእህል ማከማቻ ቦታ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች የቱን ያኽል ትበልጣላችሁ!
10
የሉቃስ ወንጌል 12:29
“ስለዚህ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን?’ እያላችሁ በማሰብ አትጨነቁ።
11
የሉቃስ ወንጌል 12:28
ታዲያ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ታይቶ ነገ በእሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንዲህ አስጊጦ የሚያለብሰው ከሆነ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፥ እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም!
12
የሉቃስ ወንጌል 12:2
የተሸፈነ ነገር ሳይገለጥ አይቀርም፤ የተሰወረውም ሳይታወቅ አይቀርም።
Home
Bible
Plans
Videos