1
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:16-18
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ ነገር አመስግኑ፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ይህ ነውና።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:23-24
የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ። የሚጠራችሁ የታመነ ነው፤ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።
3
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:15
ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ እንዲሁም ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።
4
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:11
ስለዚህ እናንተ በእርግጥ እያደረጋችሁት እንዳላችሁት፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም ሌላውን ያንጸው።
5
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:14
ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አጽኑ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።
6
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:9
እግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መዳንን እንድናገኝ እንጂ ለቁጣ እንድንሆን አስቀድሞ አልመረጠንም።
7
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:5
እናንተ ሁላችሁም የብርሃን ልጆች፥ የቀንም ልጆች ናችሁና፤ ሆኖም እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም።
Home
Bible
Plans
Videos