1
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:5-6
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
አንድ እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል አንድ አስታራቂ ደግሞ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም ምስክርነት ተገቢ በሆነው በራሱ ጊዜ የቀረበ ነበር፤
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:1-2
እንግዲህ ከሁሉ በፊት እንዲደረጉ የምመክረው ነገር ቢኖር ልመናና ጸሎት፥ ምልጃና ምስጋና ስለ ሰዎች ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ እንዲሁም እግዚአብሔርን በመምሰልና በተገባ አካሄድ ሁሉ፥ ጸጥታ የሰፈነበትና ሰላማዊ የሆነ ሕይወት እንዲኖረን ስለ ነገሥታትና በከፍተኛ ሥልጣን ላይ ስላሉ ሁሉ ጸሎት እናቅርብ።
3
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:8-10
እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው። እንዲሁም ደግሞ ሴቶች ከትሕትናና ራስን ከመግዛት ጋር በሚገባ ልብስ ራሳቸውን ያስጊጡ፤ ይሁንና በቄንጠኛ የጸጉር አሠራር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሁን። ይልቁንም እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉ ሴቶች እንደሚገባ መልካም ሥራን በመሥራት ይሁን።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች