1
ኦሪት ዘዳግም 10:12-13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ ጌታ አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው? ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔርን እንድትፈራው፥ በመንገዱም ሁሉ እንድትሄድ፥ ጌታ አምላክህንም እንድትወደው፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ እንድታመልከው፥ መልካም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት እንድትጠብቅ ነው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘዳግም 10:17
ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው።
3
ኦሪት ዘዳግም 10:16
እንግዲህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ ከእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።
4
ኦሪት ዘዳግም 10:18
ወላጁን ላጣና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፥ ስደተኛውንም ስለሚወድ ምግብና ልብስ ይሰጠዋል።
5
ኦሪት ዘዳግም 10:21
ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው።
6
ኦሪት ዘዳግም 10:20
ጌታ እግዚአብሔርን ፍራ፥ እርሱንም አምልክ፥ ከእርሱም አትነጠል፥ በስሙም ማል።
7
ኦሪት ዘዳግም 10:14
እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርሷም ያለው ሁሉ የጌታ የአምላክህ ነው።
8
ኦሪት ዘዳግም 10:19
ስለዚህ፥ እናንተ በግብጽ አገር ስደተኞች ነበራችሁና፥ ስደተኛውን ውደዱ።
Home
Bible
Plans
Videos