1
መጽሐፈ ኢያሱ 10:13
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመች፥ ጨረቃም ዘገየች። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ጸንታ ቆመች፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለችም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ኢያሱ 10:12
ጌታም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ ለጌታ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ የእስራኤልም ልጆች እያዩ እንዲህ አለ፦ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”
3
መጽሐፈ ኢያሱ 10:14
ጌታ ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና ጌታ የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።
4
መጽሐፈ ኢያሱ 10:8
ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፤ ከእነርሱም አንድም ሰው የሚቋቋምህ የለም።”
5
መጽሐፈ ኢያሱ 10:25
ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፤ ጽኑ፥ አይዞአችሁ።”
Home
Bible
Plans
Videos