1
መጽሐፈ ምሳሌ 10:22
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
የጌታ በረከት ሀብታም ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርሷ ጋር አይጨምርም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 10:19
በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 10:12
ጥላቻ ክርክርን ታስነሣለች፥ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ትከድናለች።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 10:4
የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፥ የትጉ እጅ ግን ሀብታም ታደርጋለች።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 10:17
ተግሣጽን የሚጠብቅ በሕይወት መንገድ ይሄዳል፥ ዘለፋን የሚተው ግን ይስታል።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 10:9
ያለ ነውር የሚመላለስ ተማምኖ ይሄዳል፥ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 10:27
ጌታን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፥ የከፉዎች ዕድሜ ግን ታጥራለች።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 10:3
ጌታ የጻድቁን ነፍስ አያስርብም፥ የክፉዎችን ምኞት ግን ይገለብጣል።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 10:25
ዐውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው አይገኝም፥ ጻድቅ ግን የዘለዓለም መሠረት ነው።
Home
Bible
Plans
Videos