1
መጽሐፈ ምሳሌ 15:1
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፥ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታስነሣለች።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 15:33
ጌታን መፍራት የጥበብ ትምህርት ነው፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 15:4
ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፥ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 15:22
ምክር ከሌለች የታሰበው ሳይሳካ ይቀራል፥ መካሮች በበዙበት ግን ይጸናል።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 15:13
ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል፥ በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 15:3
የጌታ ዐይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፥ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 15:16
ጌታን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 15:18
ቁጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፥ ትዕግሥተኛ ሰው ግን ጸጥ ያሰኘዋል።
9
መጽሐፈ ምሳሌ 15:28
የጻድቅ ልብ መልሱን ያስባል፥ የኀጥኣን አፍ ግን ክፋትን ያፈልቃል።
Home
Bible
Plans
Videos