1
መጽሐፈ ምሳሌ 17:17
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፥ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ምሳሌ 17:22
ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፥ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።
3
መጽሐፈ ምሳሌ 17:9
ኃጢአትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፥ ነገርን የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆቹን ይለያያል።
4
መጽሐፈ ምሳሌ 17:27
ጥቂት ቃልን የሚናገር አዋቂ ነው፥ መንፈሱም ቀዝቃዛ የሆነ አስተዋይ ነው።
5
መጽሐፈ ምሳሌ 17:28
ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፥ ከንፈሩንም የሚቈልፍ፦ ባለ አእምሮ ነው ይባላል።
6
መጽሐፈ ምሳሌ 17:1
ጥል ባለበት ዘንድ ግብዣ ከሞላበት ቤት ይልቅ በጸጥታ ደረቅ ቁራሽ ይሻላል።
7
መጽሐፈ ምሳሌ 17:14
የጠብ መጀመሪያ እንደ ውኃ አፈሳሰስ ነው፥ ስለዚህ ጠብ ሳይበረታ አንተ ክርክርን ተው።
8
መጽሐፈ ምሳሌ 17:15
ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ የሚፈርድ፥ ሁለቱ በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው።
Home
Bible
Plans
Videos