1
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1:27
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ሊያሳፍር የዚህን ዓለም ሰነፎች መረጠ፤ ኀይለኞችንም ያሳፍር ዘንድ እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ደካሞች መረጠ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1:18
የመስቀሉ ነገር በሚጠፉ ሰዎች ዘንድ ስንፍና ነውና፥ ለምንድነው ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው።
3
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1:25
የእግዚአብሔር ስንፍና ከሰው ይልቅ ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።
4
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1:9
ከልጁ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።
5
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1:10
ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ።
6
ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1 1:20
እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው? ጸሓፊስ ማን ነው? ይህን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን?
Home
Bible
Plans
Videos