1
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:11
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
እኔ ሕያው ነኝና ኀጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኀጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:7
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ፤ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው።
3
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:9
ነገር ግን ከመንገዱ ይመለስ ዘንድ ኀጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው፥ እርሱም ከመንገዱ ባይመለስ፥ በኀጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ነፍስህን ታድናለህ።
4
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:6
ጕበኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለከቱንም ባይነፋ፥ ሕዝቡንም ባያስጠነቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኀጢአቱ ተወስዶአል፤ ደሙን ግን ከጕበኛው እጅ እፈልጋለሁ።
5
ትንቢተ ሕዝቅኤል 33:5
የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ስላልተጠነቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ ቢጠነቀቅስ ኖሮ ነፍሱን በአዳነ ነበር።
Home
Bible
Plans
Videos