1
ኦሪት ዘፍጥረት 37:5
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
ዮሴፍም ሕልምን አለመ፤ ለወንድሞቹም ነገራቸው።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘፍጥረት 37:3
ያዕቆብም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወድደው ነበር፤ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና። በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።
3
ኦሪት ዘፍጥረት 37:4
ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወድደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም።
4
ኦሪት ዘፍጥረት 37:9
ደግሞም ሌላ ሕልምን አየ፤ ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም እንዲህ ነው፦ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ይሰግዱልኝ ነበር።”
5
ኦሪት ዘፍጥረት 37:11
ወንድሞቹም ቀኑበት፤ አባቱ ግን ይህን ነገር በልቡ ይጠብቀው ነበር።
6
ኦሪት ዘፍጥረት 37:6-7
እርሱም አላቸው፥ “እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፤ እነሆ፥ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች በዙርያ ከብበው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”
7
ኦሪት ዘፍጥረት 37:20
ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፤ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ሕልሞቹም ምን እንደሚሆኑ እናያለን።”
8
ኦሪት ዘፍጥረት 37:28
እነዚያ ይስማኤላውያን ነጋዴዎችም ሲያልፉ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ ጐትተው አወጡት፤ ለይስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።
9
ኦሪት ዘፍጥረት 37:19
አንዱም ለአንዱ እንዲህ አለው፥ “ያ ባለ ሕልም ይኸው መጣ።
10
ኦሪት ዘፍጥረት 37:18
እነርሱም ወደ እነርሱ ሳይቀርብ ከሩቅ አስቀድመው አዩት፥ ይገድሉትም ዘንድ በእርሱ ላይ ተማከሩ።
11
ኦሪት ዘፍጥረት 37:22
ሮቤልም፥ “ደም አታፍስሱ፤ በዚች ምድረ በዳ ባለችው ጕድጓድ ጣሉት፤ ነገር ግን እጃችሁን አትጣሉበት” አላቸው። ሮቤልም እንዲህ ማለቱ ከእጃቸው ሊያድነውና ወደ አባቱ ሊመልሰው ነው።
Home
Bible
Plans
Videos