1
የዮሐንስ ራእይ 19:7
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ፤ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
የዮሐንስ ራእይ 19:16
በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም አለው።
3
የዮሐንስ ራእይ 19:11
ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አምባላይ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።
4
የዮሐንስ ራእይ 19:12-13
ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።
5
የዮሐንስ ራእይ 19:15
አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።
6
የዮሐንስ ራእይ 19:20
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች