1
ኦሪት ዘጸአት 11:1
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
እግዚአብሔርም ሙሴን፦ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ ገና አንዲት መቅሰፍት አመጣለሁ፤ ከዚያ ወዲያም ይለቅቃችኋል፤ ሲለቅቃችሁም አባርሮ ይሰድዳችኋል።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ኦሪት ዘጸአት 11:5-6
በግብፅም አገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙፋኑ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ በኵር ድረስ፥ የከብቱም በኵር ሁሉ ይሞታል። በግብፅም አገር ሁሉ አስቀድሞ እንደ እርሱ ያልሆነ ኋላም ደግሞ የማይሆን ታላቅ ጩኸት ይሆናል።
3
ኦሪት ዘጸአት 11:9
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ተአምራቴ በግብፅ አገር ብዙ እንዲሆን ፈርዖን አይሰማችሁም፤” አለው።
Home
Bible
Plans
Videos