1
መጽሐፈ ኢያሱ 10:13
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
መጽሐፈ ኢያሱ 10:12
እግዚአብሔርም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ እግዚአብሔርን ተናገረ፥ በእስራኤልም ፊት እንዲህ አለ፦ በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፥
3
መጽሐፈ ኢያሱ 10:14
እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበረና እግዚአብሔር የሰውን ቃል የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም።
4
መጽሐፈ ኢያሱ 10:8
እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአቸዋለሁና አትፍራቸው፥ ከእነርሱም አንድ ሰው የሚቋቋምህ የለም አለው።
5
መጽሐፈ ኢያሱ 10:25
ኢያሱም፦ እግዚአብሔር በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፥ ጽኑ፥ አይዞአችሁ አላቸው።
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች