1
ሉቃስ 3:21-22
አዲሱ መደበኛ ትርጒም
ሕዝቡ ሁሉ ከተጠመቀ በኋላ ኢየሱስም ተጠመቀ፤ እየጸለየም ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በአካላዊ ቅርጽ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ ከሰማይም፣ “የምወድድህ ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ መጣ።
አወዳድር
{{ጥቅስ}} ያስሱ
2
ሉቃስ 3:16
ዮሐንስ ለሁሉም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እኔም የእርሱን የጫማ ማሰሪያ መፍታት የሚገባኝ አይደለሁም፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤
3
ሉቃስ 3:8
እንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ ደግሞም በልባችሁ፣ ‘አብርሃም አባታችን አለን’ ማለትን አትጀምሩ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።
4
ሉቃስ 3:9
አሁን እንኳ ምሣር በዛፎች ሥር ተቀምጧል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራም ዛፍ ሁሉ ተቈርጦ ወደ እሳት ይጣላል።”
5
ሉቃስ 3:4-6
ይኸውም፣ ነቢዩ ኢሳይያስ በመጽሐፉ እንዲህ ሲል በጻፈው ቃል መሠረት ነበር፤ “በበረሓ እንዲህ ብሎ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጐዳናውንም አቅኑ፤ ሸለቆው ሁሉ ይሞላል፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማው መንገድ ቀና፣ ሸካራውም ጐዳና ትክክል ይሆናል፤ የሰውም ዘር ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያል።’ ”
Home
Bible
Plans
Videos