የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

2 ቆሮንቶስ 13

13
የመጨረሻ ምክር
1ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ መሆኑ ነው፤ “ነገር ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ስለሚጸና።”#13፥1 ዘዳ 19፥15 2በሁለተኛው ጕብኝቴ እናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜ አስጠንቅቄአችሁ ነበር፤ አሁንም በሩቅ ሆኜ እንደ ገና አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ወደ እናንተም ተመልሼ ስመጣ፣ ከዚህ በፊት ኀጢአት ለሠሩትም ሆነ ለሌሎች አልራራላቸውም፤ 3ይህም የሚሆነው ክርስቶስ በእኔ ዐድሮ እንደሚናገር ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው። እርሱም በመካከላችሁ ብርቱ እንጂ ደካማ አልነበረም። 4የተሰቀለው በድካም ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር ኀይል ሕያው ሆኖ ይኖራል። እኛም በርሱ ደካሞች ብንሆንም፣ እናንተን ለማገልገል ግን በእግዚአብሔር ኀይል ከርሱ ጋራ ሕያዋን ሆነን እንኖራለን።
5በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን? 6እኛ ግን ብቁ መሆናችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ። 7አሁንም ምንም ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም እኛ ብቁዎች እንደ ሆንን ሰዎች እንዲያዩልን አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም እንኳ ብቁዎች ባንሆንም እናንተ መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው። 8ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልምና። 9እኛ ደካሞች ስንሆን፣ እናንተ ግን ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናል፤ ጸሎታችንም እናንተ ፍጹማን እንድትሆኑ ነው። 10ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኀይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።
የመጨረሻ ሰላምታ
11በተረፈ ወንድሞች ሆይ፤ ደኅና ሁኑ፤ ፍጹማን ሁኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ አንድ ሐሳብ ይኑራችሁ፤ በሰላምም ኑሩ። የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋራ ይሆናል።
12በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።
13ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
14የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።

Currently Selected:

2 ቆሮንቶስ 13: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ