2 ሳሙኤል 8
8
ዳዊት የተቀዳጃቸው ድሎች
8፥1-14 ተጓ ምብ – 1ዜና 18፥1-13
1ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቍጥጥሩም ሥር አዋላቸው፤ ሜቴግ አማ የተባለችውንም ከተማ ከፍልስጥኤማውያን ቍጥጥር ነጻ አደረጋት።
2እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።
3ከዚህም በቀር ዳዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛት መልሶ ለመያዝ በሄደ ጊዜ፣ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ወጋው። 4ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኞችና#8፥4 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም (እንዲሁም የሙት ባሕር ጥቅልሎችና 1ዜና 18፥4 ይመ) ከዚህ ጋራ ይስማማሉ፤ የማሶሬቱ ቅጅ ግን፣ ሰባት መቶ ሠረገለኞቹን ይላል። ሃያ ሺሕ እግረኞች ማረከበት። ቍጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ።
5ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺሕ ሰው ገደለ። 6ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።
7ዳዊት የአድርአዛር ሹማምት ያነገቧቸውን የወርቅ ጋሻዎች ወስዶ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። 8ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና#8፥8 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕሞች (እንዲሁም 1ዜና 18፥8 ይመ)፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ ቴባ ይላሉ። ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ አጋዘ።
9የሐማት ንጉሥ ቶዑ፣ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሰራዊት ማሸነፉን በሰማ ጊዜ፣ 10ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፣ ሰላምታና በአድርአዛር ላይ ስለ ተቀዳጀውም ድል የደስታ መግለጫ እንዲያቀርብለት፣ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።
11ንጉሥ ዳዊትም፣ ቀድሞ ካስገበራቸው መንግሥታት ሁሉ በገባለት ብርና ወርቅ እንዳደረገው፣ እነዚህንም ዕቃዎች ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው። 12የገበሩትም መንግሥታት ኤዶምና#8፥12 አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምና የሱርስቱ ቅጅ ከዚህ ጋራ ይስማማሉ (እንዲሁም 1ዜና 18፥11 ይመ)፤ አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ አራም ይላሉ። ሞዓብ፣ አሞናውያን፣ ፍልስጥኤማውያንና አማሌቃውያን ነበሩ። እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር የወሰደውን ምርኮ ለእግዚአብሔር ቀደሰ።
13ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ኤዶማውያንን#8፥13 ጥቂት የዕብራይስጥ ቅጆች፣ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕምና የሱርስቱ ቅጅ (እንዲሁም 1ዜና 18፥11 ይመ)፤ ከዚህ ጋራ ይስማማል አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን፣ አራም ይላሉ። ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ።
14በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያንም ሁሉ ለዳዊት ተገዙ፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው።
የዳዊት ሹማምት
8፥15-18 ተጓ ምብ – 1ዜና 18፥14-17
15ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕና ርትዕ አሰፈነላቸው። 16የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሰራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሓፊ ነበረ። 17እንዲሁም የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሓፊ ነበረ፤ 18የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች#8፥18 ወይም ካህናት የበላይ ሹማምት ተብሎ መተርጐም ይችላል። ነበሩ።
Currently Selected:
2 ሳሙኤል 8: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.