ሐዋርያት ሥራ 7
7
እስጢፋኖስ በሸንጎው ፊት ያደረገው ንግግር
1ሊቀ ካህናቱም፣ “ይህ የቀረበብህ ክስ እውነት ነውን?” አለው።
2እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፤ አድምጡኝ! አባታችን አብርሃም ወደ ካራን ከመምጣቱ በፊት፣ ገና በመስጴጦምያ ሳለ፣ የክብር አምላክ ተገልጦለት፣ 3‘ከአገርህና ከወገንህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ’ አለው።
4“እርሱም ከከለዳውያን ምድር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ። ከአባቱም ሞት በኋላ፣ አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት ወደዚህ አገር አመጣው። 5በዚህም ስፍራ አንዲት ጫማ ታኽል እንኳ ርስት አልሰጠውም፤ ነገር ግን በዚያ ጊዜ ምንም ልጅ ሳይኖረው፣ እርሱና ከርሱም በኋላ ዘሩ ምድሪቱን እንደሚወርሱ እግዚአብሔር ቃል ገባለት። 6ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረው፤ ‘ዘርህ በባዕድ አገር መጻተኛ ይሆናል፤ አራት መቶ ዓመትም በባርነት ተረግጦ ይገዛል። 7ነገር ግን በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እኔ ደግሞ እቀጣዋለሁ፤’ ደግሞም ‘ከዚያም አገር ወጥተው በዚህ ስፍራ ያመልኩኛል።’ ይላል እግዚአብሔር። 8ከዚያም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም ይሥሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው። ይሥሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የነገድ አባቶች ወለደ።
9“የነገድ አባቶችም በዮሴፍ ቀንተው በባርነት ወደ ግብጽ ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከርሱ ጋራ ስለ ነበር፣ 10ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽም ንጉሥ በፈርዖን ፊት ሞገስና ጥበብን አጐናጸፈው፤ ፈርዖንም በግብጽና በቤተ መንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሾመው።
11“በዚያ ጊዜም በግብጽና በከነዓን አገር ሁሉ ታላቅ መከራን ያስከተለ ራብ መጣ፤ አባቶቻችንም የሚበሉትን ዐጡ። 12ያዕቆብም እህል በግብጽ መኖሩን በሰማ ጊዜ፣ አባቶቻችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ግብጽ ላካቸው፤ 13ለሁለተኛ ጊዜ ሲሄዱ ደግሞ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ ገለጠ፤ ፈርዖንም ስለ ዮሴፍ ዘመዶች ተረዳ። 14ከዚህ በኋላ፣ ዮሴፍ ልኮ አባቱን ያዕቆብንና ሰባ ዐምስት ነፍስ የሚሆኑ ቤተ ዘመዶቹን በሙሉ አስመጣ። 15ያዕቆብ ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም አባቶቻችንም በዚያ ሞቱ። 16አስከሬናቸውም ወደ ሴኬም ተወስዶ፣ አብርሃም ከዔሞር ልጆች ላይ በጥሬ ብር በገዛው መቃብር ተቀበረ።
17“እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብም፣ በግብጽ የነበረው የሕዝባችን ቍጥር እየበዛ ሄደ። 18ከዚያ በኋላ ‘ስለ ዮሴፍ የማያውቅ አዲስ ንጉሥ በግብጽ ነገሠ።’ 19እርሱም ሕዝባችንን በተንኰሉ አስጨነቀ፤ ገና የተወለዱ ሕፃናታቸውም ይሞቱ ዘንድ ወደ ውጭ አውጥተው እንዲጥሏቸው አስገደዳቸው።
20“በዚህ ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘ ውብ ሕፃን#7፥20 ወይም ተራ ልጅ አልነበረም ነበር። በአባቱም ቤት ሦስት ወር በእንክብካቤ አደገ። 21ወደ ውጭ በተጣለም ጊዜ የፈርዖን ልጅ አግኝታ ወሰደችው፤ እንደ ራሷ ልጅ አድርጋም አሳደገችው። 22ሙሴም የግብፆችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በንግግሩና በተግባሩም ብርቱ ሆነ።
23“ሙሴ አርባ ዓመት በሆነው ጊዜ፣ ወንድሞቹን የእስራኤልን ልጆች ሊጐበኝ በልቡ ዐሰበ። 24እርሱም፣ አንድ ግብጻዊ ከወገኖቹ አንዱን በደል ሲያደርስበት አይቶ ግብጻዊውንም ገደለ፤ ለተገፋው ወገኑም ተበቀለ። 25ወገኖቹም እግዚአብሔር በርሱ እጅ ነጻ እንደሚያወጣቸው የሚያስተውሉ መስሎት ነበር፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም። 26በማግስቱም ደግሞ ሁለት እስራኤላውያን ሲጣሉ ደረሰ፤ ሊያስታርቃቸውም ፈልጎ፣ ‘ሰዎች፤ እናንተ እኮ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እንዴት እርስ በርሳችሁ ትጐዳዳላችሁ?’ አላቸው።
27“በባልንጀራው ላይ በደል ሲያደርስ የነበረው ሰው ግን፣ ሙሴን ገፈተረውና እንዲህ አለ፤ ‘አንተን በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? 28ትናንት ግብጻዊውን እንደ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋልህን?’ 29ሙሴም ይህን እንደ ሰማ ሸሽቶ በምድያም አገር መጻተኛ ሆኖ ተቀመጠ፤ በዚያም ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።
30“ከአርባ ዓመት በኋላ፣ በሲና ተራራ አካባቢ ባለው ምድረ በዳ፣ በቍጥቋጦው ውስጥ በሚንቀለቀል የእሳት ነበልባል መልአክ ተገለጠለት። 31ሙሴም ባየው ነገር ተደነቀ፤ ነገሩን ለማጣራት ወደዚያ ሲቀርብ የጌታ ድምፅ፤ 32‘እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይሥሐቅ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ’ ሲል ሰማ። ሙሴም በፍርሀት ተዋጠ፤ ለመመልከትም አልደፈረም።
33“ጌታም እንዲህ አለው፤ ‘የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች ስለ ሆነች ጫማውን ከእግርህ አውልቅ፤ 34በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በርግጥ አይቻለሁ፤ የጭንቅ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁ። አሁንም ና፤ ወደ ግብጽ መልሼ እልክሃለሁ።’
35“እንግዲህ እነዚያ፣ ‘አንተን ገዥና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው?’ ብለው የናቁትን ይህን ሙሴ እግዚአብሔር በቍጥቋጦው ውስጥ በታየው መልአክ አማካይነት ገዥና ታዳጊ አድርጎ ወደ እነርሱ ላከው። 36እርሱም መርቶ ከግብጽ አወጣቸው፤ በግብጽ፣ በቀይ ባሕርና በምድረ በዳ አርባ ዓመት ድንቅ ነገሮችንና ታምራዊ ምልክቶችን አደረገ።
37“የእስራኤልንም ልጆች፣ ‘እግዚአብሔር እንደ እኔ ያለ ነቢይ ከወንድሞቻችሁ መካከል ያስነሣላችኋል’ ያላቸው ይኸው ሙሴ ነበር። 38እርሱም በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋራ በምድረ በዳ በሕዝቡ ጉባኤ መካከል ነበር፤ የሕይወትንም ቃል ወደ እኛ ለማስተላለፍ ተቀበለ።
39“አባቶቻችን ግን ተቃወሙት እንጂ ሊታዘዙት ስላልፈለጉ በልባቸው ወደ ግብጽ ተመለሱ። 40አሮንንም፣ ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅምና!’ አሉት። 41በዚያ ጊዜ የጥጃ ምስል ሠርተው፣ ለጣዖቱ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በእጃቸውም ሥራ ተደሰቱ፤ ፈነጠዙም። 42እግዚአብሔር ግን ከእነርሱ ዘወር አለ፤ ያመልኳቸውም ዘንድ ለሰማይ ከዋክብት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ይህም በነቢያት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት ተፈጸመ፤
“ ‘እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፤ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣
መሥዋዕትንና ቍርባንን አቅርባችሁልኝ ነበርን?
43ይልቁንም ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን፣
የሞሎክን ድንኳንና የኮከብ አምላክ የሆነውን የሬምፋም ጣዖት አንሥታችሁ ተሸከማችሁ።
ስለዚህ ከባቢሎን ማዶ እንድትጋዙ አደርጋለሁ።’
44“እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው ንድፍና ባዘዘው መሠረት የተሠራችው የምስክር ድንኳን፣ ከአባቶቻችን ጋራ በምድረ በዳ ነበረች። 45አባቶቻችንም ድንኳኗን ከተቀበሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር በኢያሱ መሪነት ያሳደዳቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ ይዘዋት ገቡ፤ እስከ ዳዊትም ዘመን ድረስ በምድሪቱ ተቀመጠች፤ 46ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ በማግኘቱ ለያዕቆብ#7፥46 አንዳንድ የጥንት ቅጆች የያዕቆብ ቤት ይላሉ። አምላክ ማደሪያ ያዘጋጅ ዘንድ ለመነ፤ 47ነገር ግን የማደሪያውን ቤት የሠራለት ሰሎሞን ነበር።
48“ይሁን እንጂ፣ ልዑል የሰው እጅ በሠራው ቤት ውስጥ አይኖርም፤ ይህም ነቢዩ እንዲህ ባለው መሠረት ነው፤
49“ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤
ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤
ታዲያ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ?
ይላል ጌታ፤
ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?
50እነዚህን ነገሮች ሁሉ እጄ አልሠራችምን?’
51“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ። 52ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን እንኳ ገድለዋል፤ እናንተም አሁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም፤ 53በመላእክት አማካይነት የተሰጣችሁንም ሕግ ተቀበላችሁ እንጂ አልጠበቃችሁትም።”
የእስጢፋኖስ መወገር
54በሸንጎው ስብሰባ ላይ የነበሩትም ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ፤ ጥርሳቸውንም አፋጩበት። 55እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንዲሁም ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፣ 56“እነሆ፤ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ” አለ።
57በዚህ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ጆሯቸውን ደፍነው እርሱ ወደ አለበት በአንድነት ሮጡ፤ 58ይዘውም ከከተማው ውጭ ጣሉት፤ በድንጋይም ይወግሩት ጀመር። ይህ በሚሆንበት ጊዜ በዚያ የነበሩ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በተባለ ጕልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ።
59እስጢፋኖስም እየወገሩት ሳለ፣ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ነፍሴን ተቀበላት፤” ብሎ ጸለየ፤ 60ከዚያም ተንበርክኮ በታላቅ ድምፅ፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህን ኀጢአት አትቍጠርባቸው!” ብሎ ጮኸ፤ ይህን ካለ በኋላም አንቀላፋ።
Currently Selected:
ሐዋርያት ሥራ 7: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.