ዘፀአት 15
15
የሙሴና የማርያም መዝሙር
1ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤
“ከፍ ከፍ ብሎ ከብሯልና፣
ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤
ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣
በባሕር ውስጥ ጥሏልና።
2“እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤
ድነቴም ሆነልኝ፤
እርሱ አምላኬ ነው፤ አመሰግነዋለሁ፤
የአባቴ አምላክ ነው፤ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
3 እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፤
ስሙም እግዚአብሔር ነው።
4የፈርዖንን ሠረገሎችና ሰራዊት፣
ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤
ምርጥ የሆኑት የፈርዖን ሹማምት፣
ቀይ ባሕር ውስጥ ሰጠሙ።
5ቀላያትንም ለበሱ፤
እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረዱ።
6አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤
ቀኝ እጅህ በግርማ ከበረ፤
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤
ቀኝ እጅህ ጠላትን አደቀቀ።
7“በግርማህ ታላቅነት፣
የተቃወሙህን ጣልሃቸው፤
ቍጣህን ሰደድህ፤
እንደ ገለባም በላቸው።
8በአፍንጫህ እስትንፋስ፣
ውሆች ተቈለሉ፤
ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤
የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ።
9ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፤
እማርካቸዋለሁ፤
ምርኮን እካፈላለሁ፤
ነፍሴ በእነርሱ ትጠግባለች፤
ሰይፌን እመዝዛለሁ፤
እጄም ትደመስሳቸዋለች አለ።’
10አንተ ግን እስትንፋስህን አነፈስህ፤
ባሕርም ከደናቸው፤
በኀያላን ውሆች፣
እንደ ብረት ሰጠሙ።
11አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤
ከአማልክት መካከል፣ እንደ አንተ ማን አለ?
በቅድስናው የከበረ፣
በክብሩ የሚያስፈራ፣
ድንቆችን የሚያደርግ፣
እንደ አንተ ማን አለ?
12“ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤
ምድርም ዋጠቻቸው።
13በማይለወጠው ፍቅርህ፣
የተቤዠሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤
እነርሱን በብርታትህ፣
ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ።
14አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤
የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል።
15የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤
የሞዓብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤
የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ።
16አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህ
እስከሚያልፉ ድረስ፣
የተቤዠሃቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣
ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤
በክንድህ ብርታት፣
እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
17 እግዚአብሔር ሆይ፤ ማደሪያህ
እንዲሆን በሠራኸው ስፍራ፣
ጌታ ሆይ፤ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣
በርስትህ ተራራ ላይ፣ ታመጣቸዋለህ፤ ትተክላቸዋለህም።
18“እግዚአብሔር፣
ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”
19የፈርዖን ፈረሶች፣ ሠረገሎቹና#15፥19 ወይም፣ ሠረገለኞች ፈረሰኞቹ ወደ ባሕሩ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሃ በላያቸው ላይ መለሰባቸው፤ እስራኤላውያን ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተሻገሩ። 20ከዚያም የአሮን እኅት ነቢዪቱ ማርያም ከበሮዋን አንሥታ ያዘች፤ የቀሩትም ሴቶች ሁሉ ከበሮ ይዘው እያሸበሸቡ ተከተሏት። 21ማርያምም፣
“ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣
በባሕር ውስጥ ጥሏል፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
እጅግ ከፍ ከፍ ብሏልና”
እያለች ዘመረችላቸው።
የማራና የኤሊም ውሃ
22ከዚያም ሙሴ እስራኤልን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ፤ ለሦስት ቀናት ውሃ ሳያገኙም በምድረ በዳ ተጓዙ። 23ማራ በደረሱ ጊዜ ውሃው መራራ ስለ ነበር ሊጠጡት አልቻሉም፤ ቦታው ማራ ተብሎ የተጠራውም ከዚህ የተነሣ ነው።#15፥23 ማራ ማለት መራራ ማለት ነው። 24ሕዝቡም በሙሴ ላይ በማጕረምረም፣ “ምን እንጠጣ?” አሉ።
25ከዚያም ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ እግዚአብሔር አንዲት ዛፍ አሳየው፤ ዕንጨቷንም ወደ ውሃው ጣላት፤ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ።
በዚያም እግዚአብሔር ሕግና ሥርዐት አበጀላቸው፤ በዚያም ስፍራ ፈተናቸው። 26እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብጻውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
27ከዚያም ዐሥራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ወዳሉበት ወደ ኤሊም መጡ፤ እነርሱም በውሃው አጠገብ በዚያ ሰፈሩ።
Currently Selected:
ዘፀአት 15: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.