ሕዝቅኤል 30
30
ስለ ግብጽ የወጣ ሙሾ
1ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘ዋይ! በል፤ እንዲህም በል፤
“ወዮ ለዚያ ቀን!”
3ቀኑ ቅርብ ነው፤
የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤
የደመና ቀን፣
ለአሕዛብም የጥፋት ቀን ነው።
4በግብጽ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤
በኢትዮጵያም#30፥4 የላይኛውን የአባይ ወንዝ አካባቢን ያመላክታል። ላይ ጭንቀት ይመጣል።
የታረዱት በግብጽ ሲወድቁ፣
ሀብቷ ይወሰዳል፤
መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።
5ኢትዮጵያና ፉጥ፣ ሉድም መላው ዐረብ፣ ሊብያና#30፥5 ዕብራይስጡ ኩብ ይላል። የቃል ኪዳኑ ምድር ሕዝብ ከግብጽ ጋራ በአንድነት በሰይፍ ይወድቃሉ።
6“ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘የግብጽ ተባባሪዎች ይወድቃሉ።
የምትኵራራበት ብርታቷ ይወድቃል።
ከሚግዶል እስከ አስዋን፣
በውስጧ በሰይፍ ይወድቃሉ፤
ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
7በባድማ መሬቶች መካከል፣
ባድማ ይሆናሉ፤
ከተሞቻቸውም፣
ከፈራረሱ ከተሞች መካከል ይሆናሉ።
8በግብጽ ላይ እሳት ስጭር፣
ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቅቁ፣
በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
9“ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ያለ ሥጋት ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብጽ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በርግጥ ይመጣልና።
10“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፣
ስፍር ቍጥር የሌለውን የግብጽን ሕዝብ እደመስሳለሁ።
11ከአሕዛብ ሁሉ እጅግ ጨካኝ የሆኑት፣ እርሱና ሰራዊቱ፣
ምድሪቱን ለማጥፋት እንዲመጡ ይደረጋል፤
ሰይፋቸውን በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ፤
ምድሪቱንም ሬሳ በሬሳ ያደርጋሉ፤
12የአባይን ወንዝ ውሃ አደርቃለሁ፤
ምድሪቱን ለክፉ ሰዎች እሸጣለሁ፤
በባዕዳን እጅ፣ ምድሪቷንና በውስጧ
ያለውን ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤
እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።
13“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘ጣዖታትን አጠፋለሁ፤
በሜምፊስ#30፥13 ዕብራይስጡ ኖፍ ይለዋል፤ እንዲሁም በ16 ያሉትን ምስሎች እደመስሳለሁ።
ከእንግዲህ በግብጽ ገዥ አይኖርም፣
በምድሪቱም ላይ ፍርሀት እሰዳለሁ።
14ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤
በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤
በቴብስ#30፥14 ዕብራይስጡ ኖ ይለዋል፤ እንዲሁም በ15 እና 16 ላይ ቅጣት አመጣለሁ።
15የግብጽ ምሽግ በሆነችው፣
በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤
ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ።
16በግብጽ ላይ እሳት አነድዳለሁ፤
ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤
ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤
ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።
17የሄልዮቱ#30፥17 የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ሄሊዮት ይላል። የቡባስቱ#30፥17 ዕብራይስጡ ፊ ቢሴት ይላል ጕልማሶች፣
በሰይፍ ይወድቃሉ፤
ከተሞቹ ራሳቸውም ይማረካሉ።
18የግብጽን ቀንበር በምሰብርበት ጊዜ፣
በጣፍናስ ቀኑ ይጨልማል፤
ከዚያም የተኵራራችበት ብርታት ይንኰታኰታል።
በደመና ትሸፈናለች፤
መንደሮቿም ይማረካሉ።
19ስለዚህ በግብጽ ላይ ቅጣቴን አመጣለሁ፤
እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”
20በዐሥራ አንደኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር በሰባተኛው ቀን፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 21“የሰው ልጅ ሆይ፤ የግብጽን ንጉሥ የፈርዖንን ክንድ ሰብሬአለሁ፤ ይፈወስ ዘንድ ክንዱ አልተጠገነም፤ ወይም ሰይፍ መያዝ ይችል ዘንድ እጁ በመቃ አልታሰረም። 22ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነሥቻለሁ፤ ደኅናውንና የተሰበረውን፣ ሁለቱንም ክንዶቹን እሰብራለሁ፤ ሰይፉም ከእጁ እንዲወድቅ አደርጋለሁ። 23ግብጻውያንን በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ። 24የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ ሰይፌንም አስይዘዋለሁ፤ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም በፊቱ ክፉኛ እንደ ቈሰለ ሰው ያቃስታል። 25የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ፤ የፈርዖን ክንድ ግን ይዝላል፤ ሰይፌን በባቢሎን ንጉሥ እጅ ሳስይዝ፣ እርሱም ሲነቀንቀው፣ ያኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ። 26በሕዝቦች መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
Currently Selected:
ሕዝቅኤል 30: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.