ሕዝቅኤል 45
45
የምድሪቱ አከፋፈል
1“ ‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በዕጣ በምትከፋፈሉበት ጊዜ፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ#45፥1 13 ኪሎ ሜትር ይሆናል (ቍጥር 3፣ 5 እና 6) ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ሺሕ ክንድ#45፥1 11 ሺሕ ኪሎ ሜትር የሆነውን አንዱን ክፍል፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ስፍራ አድርጋችሁ ስጡ፤ ስፍራውም በሙሉ ቅዱስ ይሆናል፤ 2ከዚሁም ዐምስት መቶ ክንድ#45፥2 265 ሜትር በዐምስት መቶ ክንድ፣ ዙሪያው ዐምሳ ክንድ#45፥2 27 ሜትር ባዶ ቦታ ቀርቶ፣ ለመቅደሱ ይሁን። 3ከተቀደሰውም ስፍራ ላይ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱም ዐሥር ሺሕ ክንድ#45፥3 5.3 ኪሎ ሜትር (በተጨማሪም ቍጥር 5) ለካ፤ በዚህም ውስጥ መቅደሱ፣ ይኸውም ቅድስተ ቅዱሳኑ ይሆናል። 4ይህም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚያገለግሉና፣ በእግዚአብሔር ፊት ለአገልግሎት ለሚቀርቡ ካህናት፣ ቅዱስ የሆነ የምድሪቱ ክፍል ይሆናል። 5ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ስፋት ያለው ስፍራ መኖሪያ ከተሞቻቸውን እንዲከትሙ#45፥5 ሰብዓ ሊቃናትም እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን በቤተ መቅደስ… ሃያ ክፍሎች በንብረትነት ይኖራቸዋል በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ ሌዋውያን ርስት ይሆናል።
6“ ‘ከተቀደሰው ስፍራ ጋራ የተያያዘ ወርዱ ዐምስት ሺሕ ክንድ#45፥6 2.7 ኪሎ ሜትር፣ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ የሆነ ቦታ ለከተማዪቱ ርስት አድርገህ ስጥ፤ ይህም ለመላው የእስራኤል ቤት ይሆናል።
7“ ‘ገዥው ከቅዱሱ ስፍራና ከከተማው ወሰን ግራና ቀኝ ርስት ይኖረዋል፤ ይህም ከምዕራብ በኩል ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ምሥራቅ በመዝለቅ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያለውን ወሰን ርዝመት ተከትሎ ለአንዱ ነገድ ከተሰጠው ርስት ጋራ ጐን ለጐን ይሄዳል። 8ይህም መሬት በእስራኤል ምድር የገዢው ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ ገዥዎቼ ሕዝቤን አይጨቍኑም፤ ነገር ግን የእስራኤል ቤት በየነገዳቸው ርስት እንዲይዙ ይፈቅዱላቸዋል።
9“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ገዦች ሆይ! ከልክ ዐልፋችኋል፤ ይብቃችሁ፤ ዐመፅንና ጭቈናን ተዉ፤ ቀናና ትክክል የሆነውን ነገር አድርጉ። የሕዝቤን ርስት መቀማት ይቅርባችሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 10ትክክለኛ ሚዛን ትክክለኛ ኢፍና#45፥10 ኢፍ የደረቅ ነገር መስፈሪያ ነው። ትክክለኛ ባዶስ#45፥10 ባዶስ የፈሳሽ ነገር መለኪያ ነው። ይኑራችሁ። 11የኢፍና የባዶሱ መመዘኛ ተመሳሳይ ይሁን፤ አንድ ባዶስ የሆሜር#45፥11 ሆሜር የደረቅ ነገር መስፈሪያ ነው። አንድ ዐሥረኛ እንዲሁም አንድ ኢፍ የሆሜር አንድ ዐሥረኛ ይሆናል፤ ሆሜር ለሁለቱም ሚዛኖች መደበኛ መለኪያ ነው። 12አንድ ሰቅል#45፥12 690 ግራም ሃያ ጌራህ የሚይዝ ይሆናል፤ በሃያ ሰቅል ላይ ሃያ ዐምስት ሰቅልና ዐሥራ ዐምስት ሰቅል ሲጨመር አንድ ምናን ይሆናል።
ልዩ ልዩ መሥዋዕትና በዓላት
13“ ‘የምታቀርቡት ልዩ መባ ይህ ነው፤ ከአንድ ሆሜር መስፈሪያ ስንዴ አንድ ስድስተኛ ኢፍ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ሆሜር ገብስ አንድ ስድስተኛ ኢፍ ነው። 14ዘይቱ በባዶስ ሲለካ፣ የተወሰነው መስፈሪያ ከእያንዳንዱ ሆሜር አንድ ዐሥረኛ ባዶስ#45፥14 2.2 ሊትር ይሆናል፤ ይኸውም ዐሥር ባዶስ ወይም አንድ ሆሜር ነው፤ ዐሥር ባዶስ ከአንድ ሆሜር ጋራ እኩል ነውና። 15እንዲሁም ውሃ ከጠገበው ከእስራኤል መሰማሪያ፣ ሁለት መቶ በግ ካለው ከእያንዳንዱ መንጋ አንድ በግ ይውሰድ። ይህ ሁሉ ለሕዝቡ ማስተስረያ ለሚሆነው ለእህል ቍርባን፣ ለሚቃጠል መሥዋዕትና ለኅብረት መሥዋዕት#45፥15 በትውፊት የድነት መሥዋዕት ይባላል። ይውላል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 16የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ይህን ልዩ መባ ለእስራኤል ገዥ ይሰጣሉ። 17በበዓላት፣ በወር መባቻና በሰንበታት፣ ለእስራኤል ቤት በተወሰኑት በዓላት ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ማቅረብ የገዢው ኀላፊነት ነው፤ ለእስራኤል ቤት ማስተስረያ እንዲሆንም የኀጢአት መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባል።’
18“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን ነውር የሌለበትን ወይፈን ውሰድ፤ መቅደሱንም አንጻው። 19ካህኑም ከኀጢአቱ መሥዋዕት ደም በመውሰድ በቤተ መቅደሱ በር መቃኖች፣ በመሠዊያው ላይኛው ዕርከን አራት ማእዘንና በውስጠኛው አደባባይ በር መቃኖች ላይ ይርጨው። 20አንድ ሰው ሳያስብ ወይም ባለማወቅ ኀጢአት ቢሠራ፤ ወር በገባ በሰባተኛው ቀን ይህን ታደርጋለህ፤ በዚህ ዐይነት ለቤተ መቅደሱ ታስተሰርያላችሁ።
21“ ‘በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ፤ ይህም ለሰባት ቀን የሚከበር ሲሆን በዚያ ጊዜ እርሾ ያልገባበት ቂጣ ትበላላችሁ። 22በዚያም ቀን ገዥው ስለ ራሱና ስለ ምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ አንድ ወይፈን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል። 23በዓሉ በሚከበርበት በሰባቱ ቀን ገዥው በየዕለቱ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ በየዕለቱም ለኀጢአት መሥዋዕት አውራ ፍየል ያቅርብ። 24ለአንዱ ወይፈን አንድ የኢፍ መስፈሪያ፣ ለአንድ አውራ በግ አንድ የኢፍ መስፈሪያ የእህል ቍርባን አድርጎ፣ ለእያንዳንዱም ኢፍ አንድ የሂን መስፈሪያ ዘይት ዐብሮ ያቅርብ።
25“ ‘በሰባተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በሚጀመረው በሰባቱ ቀን በዓል፣ ለኀጢአት መሥዋዕት፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ ለእህል ቍርባንና ለዘይቱም እንዲሁ ያቅርብ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.