ሕዝቅኤል 48
48
የምድሪቱ አከፋፈል
1“ስማቸው የተዘረዘረው ነገዶች እነዚህ ናቸው፤
“በሰሜኑ ድንበር የዳን ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የሔትሎንን መንገድ ተከትሎ እስከ ሐማት መተላለፊያ ይደርሳል። ሐጻርዔናንና ከሐማት ቀጥሎ ያለው የደማስቆ ሰሜናዊ ድንበር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ላለው ወሰኑ አንድ ክፍል ይሆናል።
2የአሴር ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የዳንን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
3የንፍታሌም ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የአሴርን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
4የምናሴ ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የንፍታሌምን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
5የኤፍሬም ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የምናሴን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
6የሮቤል ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የኤፍሬምን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
7የይሁዳ ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የሮቤልን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
8“ይሁዳን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚያዋስነው ምድር ለመባ የሚቀርብ ድርሻ ይሆናል፤ ስፋቱም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ#48፥8 13 ኪሎ ሜትር፤ በተጨማሪም በቍጥር 9፣ 10፣ 13፣ 15፣ 20 እና 21 ነው፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውም ርዝመቱ፣ ከነገዶቹ ድርሻ እንደ አንዱ ሆኖ፣ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።
9“ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የዚህ መባ ርዝመት ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ ስፋቱ ዐሥር ሺሕ ክንድ#48፥9 5.3 ኪሎ ሜትር፤ በተጨማሪም በቍጥር 10፣ 13 እና 18 ይሆናል። 10ይህ ለካህናቱ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይቆማል። 11ይህም እስራኤላውያን በሳቱ ጊዜ፣ እንደ ሳቱት ሌዋውያን ሳይስቱ ለቀሩት፣ በታማኝነት ላገለገሉኝ ለተቀደሱት ካህናት ለሳዶቃውያን ይሆናል። 12የሌዋውያንን ምድር ከሚያዋስነው፣ ከምድሪቱ ቅዱስ ድርሻ እጅግ የተቀደሰው ድርሻ ለእነርሱ ልዩ ስጦታ ይሆናል።
13“ከካህናቱም ምድር ጐን ለጐን ሌዋውያኑ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ርዝመትና ዐሥር ሺሕ ክንድ ወርድ ያለው ይዞታ ይኖራቸዋል፤ ጠቅላላ ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ ወርዱም ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል። 14ከዚህ ላይ መሸጥ ወይም መለወጥ የለባቸውም። ይህ ከምድሪቱ ሁሉ ምርጥ ስለ ሆነ፣ ወደ ሌላ እጅ አይተላለፍም፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነውና።
15“ዐምስት ሺሕ ክንድ#48፥15 2.7 ኪሎ ሜትር ወርድና ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ርዝመት ያለው የቀረው ቦታ ለከተማዪቱ የጋራ ጥቅም፣ ለቤት ሥራና ለከብት ማሰማሪያ ይውላል፤ ከተማዪቱም በመካከሉ ትሆናለች፤ 16የከተማዪቱም መጠን በሰሜን አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ#48፥16 2.4 ኪሎ ሜትር፤ በተጨማሪም በቍጥር 30፣ 32፣ 33 እና 34፣ በደቡብ አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ፣ በምሥራቅ አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ፣ የምዕራቡም እንዲሁ አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ይሆናል። 17የከተማዪቱ ከብት ማሰማሪያ ቦታ፣ በሰሜን ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ#48፥17 135 ሜትር፣ በደቡብ ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በምሥራቅ ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ፣ በምዕራብም ሁለት መቶ ዐምሳ ክንድ ይሆናል። 18ከዚህ የሚቀረው፣ የተቀደሰውን ክፍል የሚያዋስነውና በተጓዳኝ ያለው ቦታ በምሥራቅ ዐሥር ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል። ምርቱም ለከተማዪቱ ሠራተኞች ምግብ ይሆናል። 19ምድሪቱን የሚያርሱ የከተማዪቱ ሠራተኞች ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች ይመጣሉ። 20አጠቃላይ ይዞታው በአራቱም ማእዘን እኩል ሲሆን፣ እያንዳንዱ ማእዘን ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከከተማዪቱ ድርሻ ጋራ የተቀደሰውን ክፍል ልዩ መባ በማድረግ ታስቀምጣላችሁ።
21“በተቀደሰው ድርሻና በከተማዪቱ ቦታ ግራና ቀኝ ያለው ቀሪ ቦታ፣ ለገዢው ይሆናል፤ ይህም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ከሆነው ከተቀደሰው ቦታ አንሥቶ በምሥራቅ በኩል እስከ ምሥራቁ ወሰን ይዘልቃል፤ በምዕራቡም በኩል እንዲሁ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ከሆነው ይዞታ አንሥቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ይዘልቃል። የየነገዱ ድርሻ ከሆነውም መሬት ጐን ለጐን የሚሄዱት ቦታዎች የገዢው ይሆናሉ። የተቀደሰው ቦታና መቅደሱ በመካከላቸው ይሆናሉ። 22ስለዚህ የሌዋውያኑ ይዞታና የከተማዪቱ ይዞታ ለገዢው በተሰጠው ቦታ መካከል ይሆናል፤ የገዢው ቦታም በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበር መካከል ይሆናል።
23“የቀሩት ነገዶች ድርሻ እንደሚከተለው ይሆናል፤
“የብንያም ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ይዘልቃል።
24የስምዖን ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የስምዖንን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
25የይሳኮር ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የስምዖንን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
26የዛብሎን ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የይሳኮርን ምድር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
27የጋድ ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የዛብሎንን ግዛት ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያዋስናል።
28የጋድ ደቡባዊ ወሰን ከታማር ደቡብ እስከ መሪባ ቃዴስ ውሆች ይደርሳል፤ የግብጽን ደረቅ ወንዝ ይዞ እስከ ታላቁ ባሕር#48፥28 ሜድትራኒያንን ያመለክታል ይዘልቃል።
29“ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ምድር ይህች ናት፤ ድርሻዎቻቸውም እነዚህ ናቸው” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የከተማዪቱ በሮች
30“የከተማዪቱ መውጫ በሮች እነዚህ ናቸው፤
“ከሰሜን በኩል አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ርዝመት ካለው በር አንሥቶ፣ 31የከተማዪቱ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይጠራሉ፤ በሰሜን በኩል ያሉት ሦስቱ በሮች የሮቤል ነገድ በር፣ የይሁዳ ነገድ በርና የሌዊ ነገድ በር ይሆናሉ።
32በምሥራቅ በኩል አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የዮሴፍ በር፣ የብንያም በርና የዳን በር ናቸው።
33በደቡብ በኩል አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች አሉ፤ እነዚህም የስምዖን በር፣ የይሳኮር በርና የዛብሎን በር ናቸው።
34በምዕራብ በኩል አራት ሺሕ ዐምስት መቶ ክንድ ርዝመት ባለው በር ሦስት በሮች ይኖራሉ፤ እነዚህም የጋድ በር፣ የአሴር በርና የንፍታሌም በር ናቸው።
35“የከተማዪቱም ዙሪያ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ክንድ#48፥35 9.5 ኪሎ ሜትር ይሆናል፤
“የከተማዪቱ ስም፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ‘እግዚአብሔር በዚያ አለ’ ” ይሆናል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.