የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 36

36
የዔሳው ዝርያዎች
36፥10-14 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥35-37
36፥20-28 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥38-42
1ኤዶም የተባለው የዔሳው ትውልድ ይህ ነው።
2ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣ 3እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችው የእስማኤል ልጅ ቤሴሞት ነበሩ።
4ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት፤ ቤሴሞት ደግሞ ራጉኤልን ወለደችለት። 5እንደዚሁም ኦሆሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።
6ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ። 7ብዙ ሀብት ስለ ነበራቸው ዐብረው መኖር አልቻሉም፤ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም። 8ስለዚህ ኤዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።
9በሴይር ተራራማ አገር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤
10የዔሳው ወንዶች ስም፦
የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤
11የኤልፋዝ ልጆች፦
ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤ 12የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ቲምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።
13የራጉኤል ወንዶች ልጆች፦
ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህ ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።
14የፂብዖን የልጅ ልጅ፣ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት ኦሆሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦
የዑስ፣ የዕላምና ቆሬ።
15ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤
የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦
አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣ 16አለቃ ቆሬ፣#36፥16 ከማሶሬቲኩ ጽሑፍ ጋራ ተመሳሳይ ሲሆን በኦሪተ ሳምራውያን ግን (በተጨማሪ ዘፍ 36፥11 እና 1ዜና 1፥36 ይመ) ውስጥ “ቆሬ” የሚለው ቃል የለም። አለቃ ጎቶምና አለቃ አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።
17የዔሳው ልጅ ራጉኤል ልጆች፦
አለቃ ናሖት፣ አለቃ ዛራ፣ አለቃ ሣማና አለቃ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጅ ነበሩ።
18የዔሳው ሚስት የአህሊባም ልጆች፦
አለቃ የዑስ፣ አለቃ የዕላምና፣ አለቃ ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ፣ ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።
19እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።
20በዚያች ምድር ይኖሩ የነበሩ የሖሪው የሴይር ልጆች እነዚህ ነበሩ፦
ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣ 21ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
22የሎጣን ወንዶች ልጆች፦
ሖሪና ሄማን#36፥22 ሔማም የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ሖማም ለሚለው ቃል አማራጭ ትርጕም ነው (1ዜና 1፥39 ይመ)።፤ ቲምናዕ የሎጣን እኅት ነበረች።
23የሦባል ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦
ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባል፣ ሽፎና አውናም፤
24የፂብዖን ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦
አያ እና ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፂብዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍል ውሃ ምንጮችን#36፥24 ከቩልጌት ጋራ ተመሳሳይ ሲሆን ሱርስቱ ግን የተገኘ ውሃ ይለዋል፤ በዕብራይስጥ የዚህ ቃል ትርጕም አይታወቅም። በምድረ በዳ ያገኘ ሰው ነው።
25የዓና ልጆች፦
ዲሶንና የዓና ሴት ልጅ ኦሆሊባማ፤
26የዲሶን ወንዶች ልጆች፦
ሔምዳን፣ ኤስባን፣ ይትራን እና ክራን፤
27የኤጽር ወንዶች ልጆች፦
ቢልሐን፣ ዛዕዋን እና ዓቃን።
28የዲሳን ወንዶች ልጆች፦
ዑፅ እና አራን።
29የሖሪውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦
ሎጣን፣ ሦባል፣ ፂብዖን፣ ዓና፣ 30ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን።
እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
የኤዶም ነገሥታት
36፥31-43 ተጓ ምብ – 1ዜና 1፥43-54
31በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት፣#36፥31 ወይም እስራኤላዊ መንግሥት በእነርሱ ላይ ከመንገሡ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦
32የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ላይ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
33ባላቅ ሲሞት፣ የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በምትኩ ነገሠ።
34ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ።
35ሑሳም ሲሞት፣ በሞዓብ ምድር ምድያማውያንን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ። የከተማውም ስም ዓዊት ተባለ።
36ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።
37ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ#36፥37 የኤፍራጥስ ወንዝ ሊሆን ይችላል። አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኡል በምትኩ ነገሠ።
38ሳኡል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን በምትኩ ነገሠ።
39የዓክቦር ልጅ በኣልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማዪቱም ስም ፋዑ ነው፤ የሚስቱም ስም መሄጣብኤል ሲሆን፣ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።
40ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦
ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣
41ኦሆሊባማ፣ ኤላ፣ ፒኖን፣
42ቄናዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
43መግዲኤል እና ዒራም።
እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው የኤዶም ዘሮች የነገድ አለቆች ነበሩ።
ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው።

Currently Selected:

ዘፍጥረት 36: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ