ዕብራውያን 3
3
ኢየሱስ ከሙሴ በላይ ነው
1እንግዲህ የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፤ የእምነታችን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ። 2ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ ታማኝ እንደ ነበር፣ እርሱም ለሾመው ታማኝ ነበር። 3ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው፣ ኢየሱስም ከሙሴ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተገኝቷል። 4እያንዳንዱ ቤት የራሱ ሠሪ አለው፤ ነገር ግን ሁሉን የሠራ እግዚአብሔር ነው። 5“ሙሴ ወደ ፊት ስለሚነገረው ነገር እየመሰከረ፣ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ እንደ አንድ ታማኝ አገልጋይ ነበር።”#3፥5 ዘኍ 12፥7 6ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ልጅ ነው። እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።
ስለ አለማመን የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
7ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣
“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣
8በምድረ በዳ በፈተና ቀን፣
በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣
ልባችሁን አታደንድኑ።
9አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤
መረመሩኝ፤ ያደረግሁትንም ሁሉ ለአርባ ዓመት አዩ።
10በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤
እንዲህም አልሁ፤ ‘በልባቸው ዘወትር ይስታሉ፤
መንገዴንም አላወቁም።’
11ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤
‘ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም።’ ”#3፥11 መዝ 95፥7-11
12ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ። 13ነገር ግን ከመካከላችሁ ማንም በኀጢአት ተታልሎ ልቡ እንዳይደነድን፣ “ዛሬ” እየተባለ ሳለ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ። 14በመጀመሪያ የነበረንን እምነት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋራ ተካፋዮች እንሆናለን። 15ይኸውም፣
“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣
በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣
አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ”#3፥15 መዝ 95፥7፤ 8
እንደ ተባለው ነው።
16ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ ከግብጽ መርቶ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን? 17አርባ ዓመት የተቈጣውስ እነማንን ነበር? ኀጢአት ሠርተው ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረውን አይደለምን? 18ያልታዘዙትን#3፥18 ወይም ያላመኑትን ካልሆነ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ? 19እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደ ሆነ እንረዳለን።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.