ሆሴዕ 2:9-15

ሆሴዕ 2:9-15 NASV

“ስለዚህ እህሌን በመከር ጊዜ፣ አዲሱም የወይን ጠጅ በደረሰ ጊዜ እወስዳለሁ፤ ዕርቃኗንም እንዳትሸፍንበት፣ ሱፍና የሐር ልብሴን መልሼ እወስድባታለሁ። አሁንም በውሽሞቿ ፊት፣ ነውሯን እገልጣለሁ፤ ከእጄም የሚያድናት የለም። የደስታ በዓሎቿን ሁሉ፣ የዓመት በዓላቷንና የወር መባቻዎቿን፣ ሰንበቶቿንና የተመረጡ በዓላቷን ሁሉ አስቀራለሁ። ከውሽሞቼ የተቀበልሁት ዋጋ ነው የምትለውን የወይን ተክሎቿንና የበለስ ዛፎቿን አጠፋለሁ፤ ጫካ አደርገዋለሁ፤ የዱር አራዊትም ይበሉታል። ለበኣል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው ቀናት እቀጣታለሁ፤ በጌጣጌጥና በቀለበቶች ራሷን አስጊጣለች፤ ውሽሞቿንም ተከትላ ሄዳለች፤ እኔን ግን ረስታለች” ይላል እግዚአብሔር። “ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤ በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ። በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤ የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ። በዚያም ከግብጽ እንደ ወጣችበት ቀን፣ እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።