ሆሴዕ 4
4
በእስራኤል ላይ የቀረበ ክስ
1እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤
እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤
ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤
እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።
2በዚያ ያለው ርግማን#4፥2 መርገምን ያመለክታል፣ መዋሸት፣ መግደል፣
መስረቅና ማመንዘር ብቻ ነው፤
ቃል ኪዳንን ሁሉ ያፈርሳሉ፤
ደም ማፍሰስና ግድያ ይበዛል።
3ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤#4፥3 ወይም ደረቀች
በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤
የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣
የባሕርም ዓሦች ዐለቁ።
4“ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤
ማንም ሌላውን አይወንጅል፤
በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣
ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።
5ቀንና ሌሊት ትደናበራላችሁ፤
ነቢያትም ከእናንተ ጋራ ይደናበራሉ።
ስለዚህ እናታችሁን አጠፋታለሁ፤
6ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል።
ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣
እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤
የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣
እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
7ካህናት በበዙ ቍጥር በእኔ ላይ የሚያደርጉት ኀጢአት በዝቷል፤
ክብራቸውንም#4፥7 ማሶሬቲክ የሚለው እንዲሁ ሲሆን የጥንት ዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት ግን ክብሬን ይላል። በውርደት ለውጠዋል።#4፥7 ሱርስትና የጥንት ዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት የሚሉት እንዲሁ ሲሆን፣ ማሶሬቲክ ግን እለውጠዋለሁ ይላል።
8የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤
ርኩሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።
9ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤
ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤
እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።
10“ይበላሉ ግን አይጠግቡም፤
ያመነዝራሉ ግን አይበዙም፤
እግዚአብሔርን በመተው፣
ራሳቸውን 11ለአመንዝራነት፣
ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤
በእነዚህም የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ።
12ከዕንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቃሉ፤
ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።
የአመንዝራነት መንፈስ ያስታቸዋል፤
ለአምላካቸውም ታማኝ አልሆኑም።
13በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤
መልካም ጥላ ባለው፣ በወርካ፣
በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣
በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቍርባን ያቀርባሉ።
ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን፣
ምራቶቻችሁም አመንዝራዎች ይሆናሉ።
14“ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣
የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ
አልቀጣቸውም።
ወንዶች ከጋለሞቶች ጋራ ይሴስናሉ፤
ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋራ ይሠዋሉና፤
የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!
15“እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣
ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ።
“ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤
ወደ ቤትአዌንም#4፥15 ቤትአዌን የእግዚአብሔር ቤት የተባለችው ቤቴል ስትሆን፣ የቃሉ ትርጕም የክፋት ቤት ማለት ነው። አትውጡ፤
‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብላችሁም አትማሉ።
16እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣
እልኸኞች ናቸው፤
ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶች
እንዴት ያሰማራቸዋል?
17ኤፍሬም ከጣዖት ጋራ ተጣምሯል፤
እስኪ ተዉት፤
18መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣
ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤
ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወድዳሉ።
19ዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤
መሥዋዕቶቻቸውም ኀፍረት ያመጡባቸዋል።”
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
ሆሴዕ 4
4
በእስራኤል ላይ የቀረበ ክስ
1እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤
እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤
ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤
እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።
2በዚያ ያለው ርግማን#4፥2 መርገምን ያመለክታል፣ መዋሸት፣ መግደል፣
መስረቅና ማመንዘር ብቻ ነው፤
ቃል ኪዳንን ሁሉ ያፈርሳሉ፤
ደም ማፍሰስና ግድያ ይበዛል።
3ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤#4፥3 ወይም ደረቀች
በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤
የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣
የባሕርም ዓሦች ዐለቁ።
4“ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤
ማንም ሌላውን አይወንጅል፤
በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣
ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።
5ቀንና ሌሊት ትደናበራላችሁ፤
ነቢያትም ከእናንተ ጋራ ይደናበራሉ።
ስለዚህ እናታችሁን አጠፋታለሁ፤
6ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል።
ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣
እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤
የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣
እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
7ካህናት በበዙ ቍጥር በእኔ ላይ የሚያደርጉት ኀጢአት በዝቷል፤
ክብራቸውንም#4፥7 ማሶሬቲክ የሚለው እንዲሁ ሲሆን የጥንት ዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት ግን ክብሬን ይላል። በውርደት ለውጠዋል።#4፥7 ሱርስትና የጥንት ዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት የሚሉት እንዲሁ ሲሆን፣ ማሶሬቲክ ግን እለውጠዋለሁ ይላል።
8የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤
ርኩሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።
9ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤
ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤
እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።
10“ይበላሉ ግን አይጠግቡም፤
ያመነዝራሉ ግን አይበዙም፤
እግዚአብሔርን በመተው፣
ራሳቸውን 11ለአመንዝራነት፣
ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤
በእነዚህም የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ።
12ከዕንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቃሉ፤
ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።
የአመንዝራነት መንፈስ ያስታቸዋል፤
ለአምላካቸውም ታማኝ አልሆኑም።
13በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤
መልካም ጥላ ባለው፣ በወርካ፣
በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣
በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቍርባን ያቀርባሉ።
ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን፣
ምራቶቻችሁም አመንዝራዎች ይሆናሉ።
14“ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣
የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ
አልቀጣቸውም።
ወንዶች ከጋለሞቶች ጋራ ይሴስናሉ፤
ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋራ ይሠዋሉና፤
የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!
15“እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣
ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ።
“ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤
ወደ ቤትአዌንም#4፥15 ቤትአዌን የእግዚአብሔር ቤት የተባለችው ቤቴል ስትሆን፣ የቃሉ ትርጕም የክፋት ቤት ማለት ነው። አትውጡ፤
‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብላችሁም አትማሉ።
16እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣
እልኸኞች ናቸው፤
ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶች
እንዴት ያሰማራቸዋል?
17ኤፍሬም ከጣዖት ጋራ ተጣምሯል፤
እስኪ ተዉት፤
18መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣
ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤
ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወድዳሉ።
19ዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤
መሥዋዕቶቻቸውም ኀፍረት ያመጡባቸዋል።”
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.