ኢሳይያስ 11
11
ከእሴይ ግንድ የወጣ ቍጥቋጥ
1ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤
ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።
2የእግዚአብሔር መንፈስ፣
የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣
የምክርና የኀይል መንፈስ፣
የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል።
ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤
ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።
4ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤
ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤
በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤
በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
5ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣
ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።
6ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋራ ይኖራል፤
ነብርም ከፍየል ግልገል ጋራ ይተኛል፤
ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሠባ ከብት#11፥6 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን፣ የሠባ አንበሳ ይበላል ይላል። በአንድነት ይሰማራሉ፤
ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
7ላምና ድብ በአንድነት ይሰማራሉ፤
ልጆቻቸውም ዐብረው ይተኛሉ፤
አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።
8ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፤
ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጕድጓድ ይከትታል።
9በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ
ጕዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤
ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
10በዚያም ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ አሕዛብ እርሱን ይፈልጋሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል። 11በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ#11፥11 የላይኛውን የአባይ አካባቢን ያመላክታል።፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
12ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤
ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤
የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፣
ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።
13የኤፍሬም ምቀኛነት ያከትማል፤
የይሁዳ ጠላቶችም#11፥13 ወይም፣ ባላንጣዎቹ። ይቈረጣሉ፤
ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤
ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።
14በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤
ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤
በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤
አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።
15 እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣
የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤
እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ#11፥15 ዕብራይስጡ ወንዙ ይላል። ላይ ይዘረጋል፤
ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ
ይለያየዋል፤
ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።
16እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ
እንደ ሆነው ሁሉ፣
ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣
እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።
Currently Selected:
ኢሳይያስ 11: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
ኢሳይያስ 11
11
ከእሴይ ግንድ የወጣ ቍጥቋጥ
1ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤
ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።
2የእግዚአብሔር መንፈስ፣
የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣
የምክርና የኀይል መንፈስ፣
የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል።
ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤
ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።
4ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤
ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤
በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤
በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
5ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣
ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።
6ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋራ ይኖራል፤
ነብርም ከፍየል ግልገል ጋራ ይተኛል፤
ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሠባ ከብት#11፥6 ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን፣ የሠባ አንበሳ ይበላል ይላል። በአንድነት ይሰማራሉ፤
ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
7ላምና ድብ በአንድነት ይሰማራሉ፤
ልጆቻቸውም ዐብረው ይተኛሉ፤
አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።
8ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፤
ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጕድጓድ ይከትታል።
9በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ
ጕዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤
ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
10በዚያም ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ አሕዛብ እርሱን ይፈልጋሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል። 11በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ#11፥11 የላይኛውን የአባይ አካባቢን ያመላክታል።፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
12ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤
ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤
የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፣
ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።
13የኤፍሬም ምቀኛነት ያከትማል፤
የይሁዳ ጠላቶችም#11፥13 ወይም፣ ባላንጣዎቹ። ይቈረጣሉ፤
ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤
ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።
14በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤
ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤
በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤
አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።
15 እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣
የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤
እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ#11፥15 ዕብራይስጡ ወንዙ ይላል። ላይ ይዘረጋል፤
ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ
ይለያየዋል፤
ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።
16እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ
እንደ ሆነው ሁሉ፣
ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣
እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.