ኢሳይያስ 22
22
ስለ ኢየሩሳሌም የተነገረ ትንቢት
1ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ንግር፤
እስኪ ምን ቢጨንቃችሁ ነው
ሁላችሁም ሰገነት ላይ የወጣችሁት?
2አንቺ ጫጫታ የሞላብሽ ከተማ፤
የውካታና የፈንጠዝያ ከተማ ሆይ፤
የተገደሉብሽ በሰይፍ የተሠዉ አይደሉም፤
በጦርነትም አልሞቱም።
3መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤
ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤
ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣
ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል።
4ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤
አምርሬ ላልቅስበት፣
ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣
ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።
5ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር
በራእይ ሸለቆ፣
የመጯጯኺያ፣ የመረገጥና የሽብር፣
ቅጥሮችን የማፈራረስ፣
ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።
6ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣
ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤
ቂርም ጋሻዋን አነገበች።
7መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤
ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል።
8የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል።
በዚያ ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣
የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤
9የዳዊት ከተማ
ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤
በታችኛውም ኵሬ፣
ውሃ አጠራቀማችሁ።
10በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤
ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።
11ለጥንቱ ኵሬ ውሃ የሚሆን፣
በሁለቱ ቅጥሮች መካከል ውሃ ማጠራቀሚያ ሠራችሁ፤
ነገር ግን ይህን ያደረገውን አልተመለከታችሁም፤
ቀድሞ ዐቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።
12በዚያ ቀን ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣
እንድታለቅሱና በዋይታ እንድትጮኹ፣
ጠጕራችሁን እንድትነጩ
ማቅም እንድትለብሱ ጠራችሁ።
13ነገር ግን እነሆ፤ ደስታና ሐሤት፣
ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣
ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ!
“ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ!” አላችሁ።
14የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ገለጠልኝ፤ እንዲህም ሲል በጆሮዬ ሰማሁ፤ “ይህ ኀጢአት እስከምትሞቱበት ቀን ድረስ አይሰረይላችሁም” ይላል ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
15ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ሂድና ይህን መጋቢ፣
የቤቱንም ኀላፊ ሳምናስን እንዲህ በለው፤
16‘እዚህ ምን ታደርጋለህ?
በዚህ ስፍራ ለራስህ መቃብርን እንድታዘጋጅ፣
በከፍታውም ላይ መቀበሪያህን እንድትወቅር፣
ሬሳህ የሚያርፍበትንም ዐለት እንድትጠርብ ማን ፈቀደልህ?’
17“አንተ ኀያል ሰው ሆይ፤ ተጠንቀቅ፤
እግዚአብሔር አጥብቆ ሊይዝህ፣ በእጆቹም ጨብጦ ሊወረውርህ ነው።
18አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣
ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤
አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረት!
በዚያ ትሞታለህ፤
የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ።
19ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤
ከኀላፊነትህም ትባረራለህ።
20“በዚያ ቀን አገልጋዬን፣ የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፤ 21መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል። 22የዳዊትን ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም። 23በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ካስማ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን#22፥23 ወይም፣ መቀመጫ ተብሎ መተርጐም ይችላል። ይሆናል። 24የቤተ ሰቡ ክብር፣ ልጅና የልጅ ልጅ፣ እንዲሁም ከማሰሮ ጀምሮ እስከ ጋን ድረስ ያለ የቤት ዕቃ ሁሉ በርሱ ላይ ይንጠለጠላል።
25“በዚያ ቀን” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ “በአስተማማኝ ስፍራ የተተከለ ካስማ ይነቀላል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፤ በርሱም ላይ የተንጠለጠለው ሸክም ወድቆ ይከሰከሳል፤” እግዚአብሔር ይህን ተናግሯልና።
Currently Selected:
ኢሳይያስ 22: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.