ኢሳይያስ 25
25
ምስጋና ለእግዚአብሔር
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤
ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤
አስቀድሞ የታሰበውን፣
ድንቅ ነገር፣
በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና።
2ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤
የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤
የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤
ተመልሳም አትሠራም።
3ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤
የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል።
4ለድኻ መጠጊያ፣
በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣
ከማዕበል መሸሸጊያ፣
ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል።
የጨካኞች እስትንፋስ፣
ከግድግዳ ጋራ እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤
5እንደ ምድረ በዳም ትኵሳት ነው።
የባዕድን ጩኸት እረጭ ታደርጋለህ፤
ትኵሳት በደመና ጥላ እንደሚበርድ፣
የጨካኞችም ዝማሬም እንዲሁ ጸጥ ይላል።
6የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣
ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣
የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣
ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።
7በዚህም ተራራ ላይ፣
በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣
በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤
8ሞትንም ለዘላለም ይውጣል።
ጌታ እግዚአብሔር
ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤
የሕዝቡንም ውርደት
ከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤
እግዚአብሔር ተናግሯልና።
9በዚያ ቀን እንዲህ ይባላል፤
“እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤
በርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤
እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤
በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”
10የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤
ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋራ እንደሚረገጥ፣
ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል።
11ዋናተኛ ሲዋኝ እጁን እንደሚዘረጋ፣
በውስጡ ሆነው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤
ጌታ በእጃቸው ተንኰል ሳይታለል፣
ትዕቢታቸውን ያዋርዳል።
12ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤
ወደ ታች ያወርደዋል፤
ወደ ምድር አውርዶም
ትቢያ ላይ ይጥለዋል።
Currently Selected:
ኢሳይያስ 25: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
ኢሳይያስ 25
25
ምስጋና ለእግዚአብሔር
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤
ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤
አስቀድሞ የታሰበውን፣
ድንቅ ነገር፣
በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና።
2ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤
የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤
የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤
ተመልሳም አትሠራም።
3ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤
የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል።
4ለድኻ መጠጊያ፣
በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣
ከማዕበል መሸሸጊያ፣
ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል።
የጨካኞች እስትንፋስ፣
ከግድግዳ ጋራ እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤
5እንደ ምድረ በዳም ትኵሳት ነው።
የባዕድን ጩኸት እረጭ ታደርጋለህ፤
ትኵሳት በደመና ጥላ እንደሚበርድ፣
የጨካኞችም ዝማሬም እንዲሁ ጸጥ ይላል።
6የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣
ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣
የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣
ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።
7በዚህም ተራራ ላይ፣
በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣
በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤
8ሞትንም ለዘላለም ይውጣል።
ጌታ እግዚአብሔር
ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤
የሕዝቡንም ውርደት
ከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤
እግዚአብሔር ተናግሯልና።
9በዚያ ቀን እንዲህ ይባላል፤
“እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤
በርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤
እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤
በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”
10የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤
ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋራ እንደሚረገጥ፣
ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል።
11ዋናተኛ ሲዋኝ እጁን እንደሚዘረጋ፣
በውስጡ ሆነው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤
ጌታ በእጃቸው ተንኰል ሳይታለል፣
ትዕቢታቸውን ያዋርዳል።
12ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤
ወደ ታች ያወርደዋል፤
ወደ ምድር አውርዶም
ትቢያ ላይ ይጥለዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.