ኤርምያስ 2
2
የእስራኤል ሕዝብ አምላኩን መተው
1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣
በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣
በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣
እንዴት እንደ ተከተልሽኝ አስታውሳለሁ።
3እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረች፤
የመከሩም በኵር ነበረች፤
የዋጧት ሁሉ በደለኞች ሆኑ፤
መዓትም ደረሰባቸው’ ”
ይላል እግዚአብሔር።
4የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ወገን ሁላችሁ፣
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣
ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣
ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣
ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?
6እነርሱም፣ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፣
በወና ምድረ በዳ፣
በጐድጓዳና በበረሓ መሬት፣
በደረቅና በጨለማ#2፥6 ወይም በሞት ጥላ ቦታ፣
ሰው በማያልፍበትና በማይኖርበት ስፍራ
የመራን እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው አልጠየቁም።
7እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣
ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤
እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤
ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።
8‘እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው
ካህናቱ አልጠየቁም፤
ከሕጉ ጋራ የሚውሉት አላወቁኝም፤
መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤
ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤
ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ።
9“ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤
ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።”
ይላል እግዚአብሔር።
10“ወደ ኪቲም#2፥10 ኪቲም ቆጵሮስና የምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ ማለት ነው። ጠረፍ ተሻገሩና እዩ፤
ወደ ቄዳርም#2፥10 ቄዳር በሶርያዊ ዓረቢያ ምድረ በዳ የሚገኙ የበዶይን ነገዶች መኖሪያ፤ ልካችሁ በጥንቃቄ መርምሩ፣
እንዲህ ዐይነት ነገር ተደርጎ ያውቅ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤
11የእውነት አማልክት ባይሆኑም እንኳ፣
አማልክቱን የለወጠ ሕዝብ አለን?
ሕዝቤ ግን ክብራቸው#2፥11 የዕብራውያን የጥንት ጸሐፍት ትውፊት የሆነው የማሶሬቲክ ጽሑፍ ክብሬን ይላል። የሆነውን፣
በከንቱ ነገር ለወጡ።
12ሰማያት ሆይ፤ በዚህ ተገረሙ፤
በታላቅ ድንጋጤም ተንቀጥቀጡ፤”
ይላል እግዚአብሔር።
13“ሕዝቤ ሁለት ኀጢአት ፈጽመዋል፤
ሕያው የውሃ ምንጭ የሆንሁትን፣
እኔን ትተዋል፤
ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓዶች፣
ለራሳቸው ቈፍረዋል።
14እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውልድ ባሪያ?
ታዲያ፣ ስለ ምን ለብዝበዛ ተዳረገ?
15አንበሶች በርሱ ላይ አገሡ፤
በኀይለኛ ድምፅም ጮኹበት።
ምድሩን ባድማ አድርገውበታል፤
ከተሞቹ ተቃጥለዋል፤ ወናም ሆነዋል።
16ደግሞም የሜምፊስና#2፥16 ሜምፎስ በዕብራይስጡ ኖፍ ይላል፤ ወይም ጭንቅላትሽን ፈጠፈጡ ወይም ሰነጠቀ የጣፍናስ ሰዎች፣
መኻል ዐናትሽን ላጩሽ።
17በመንገድ የሚመራሽን፣
እግዚአብሔር አምላክሽን በመተውሽ፣
ይህን በራስሽ ላይ አላመጣሽምን?
18ከሺሖር#2፥18 የአባይ ወንዝ አንዱ ተነጣይ ጅረት ነው። ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣
አሁንስ ለምን ወደ ግብጽ ወረድሽ?
ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣
ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ?
19ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤
ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤
እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣
እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣
ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ
አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤”
ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
20“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰበርሁ፤
እስራትሽን በጣጠስሁ፤
አንቺም፣ ‘አላገለግልህም’ አልሽ፤
ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ሥር፣
በእያንዳንዱም ለምለም ዛፍ ሥር፣
ለማመንዘር ተጋደምሽ።
21እኔ፣ እንደ ምርጥ የወይን ተክል፣
ጤናማና አስተማማኝ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤
ታዲያ ብልሹ የዱር ወይን ተክል ሆነሽ፣
እንዴት ተለወጥሽብኝ?
22በልዩ ቅጠል ብትታጠቢ፣
ብዙ ሳሙና ብትጠቀሚም፣
የበደልሽ ዕድፍ አሁንም በፊቴ ነው፤”
ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
23“ ‘አልረከስሁም፣
በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ?
በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽ
እስኪ አስቢ፣
ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤
እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤
24በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣
በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤
ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል?
ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም
በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።
25እግርሽ እስኪነቃ አትሩጪ፤
ጕረሮሽም በውሃ ጥም እስኪደርቅ አትቅበዝበዢ።
አንቺ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤
ባዕዳን አማልክትን ወድጃለሁ፤
እነርሱን እከተላለሁ’ አልሽ።
26“ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፣
የእስራኤልም ቤት ዐፍሯል፤
እነርሱ፣ ንጉሦቻቸውና ሹሞቻቸው፣
ካህናታቸውና ነቢያታቸው እንዲሁ ያፍራሉ።
27ዛፉን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ’
ድንጋዩንም፣ ‘አንተ ወለድኸኝ’ አሉ፤
ፊታቸውን ሳይሆን፣
ጀርባቸውን ሰጥተውኛልና፤
በመከራቸው ጊዜ ግን፣
‘መጥተህ አድነን’ ይላሉ።
28ታዲያ፣ ልታመልካቸው ያበጀሃቸው አማልክት ወዴት ናቸው?
በመከራህ ጊዜ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ፣
ይሁዳ ሆይ፤ እስኪ ይምጡና ያድኑህ፤
የከተሞችህን ቍጥር ያህል፣
የአማልክትህም ብዛት እንዲሁ ነውና።
29“ለምን በእኔ ታማርራላችሁ?
ያመፃችሁብኝ እናንተ ሁላችሁ ናችሁ፤”
ይላል እግዚአብሔር።
30“ልጆቻችሁን በከንቱ ቀጣኋቸው፤
እነርሱም አልታረሙም።
ሰይፋችሁ እንደ ተራበ አንበሳ
ነቢያታችሁን በልቷል።
31“የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤
“እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣
ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን?
ሕዝቤ፣ ‘እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤
ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?
32ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣
ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን?
ሕዝቤ ግን፣
እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል።
33ፍቅርን ለመፈለግ እንዴት ሥልጡን ነሽ?
ልክስክስ ክፉ ሴቶች እንኳ ከመንገድሽ ብዙ ክፋት ይማራሉ።
34በስርቆት ያልያዝሻቸው፣
የንጹሓን ድኾች ደም፣
በልብስሽ ላይ ተገኝቷል።
ይህን ሁሉ አድርገሽም፣
35‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤
በርግጥ ቍጣው ከእኔ ርቋል’ ትያለሽ።
እኔ ግን እፈርድብሻለሁ፤
‘ኀጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና።
36መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣
ለምን ትሮጫለሽ?
አሦር እንዳዋረደሽ፣
ግብጽም እንዲሁ ያዋርድሻል።
37የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣
በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣
እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ
ከዚያም ትወጫለሽ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
ኤርምያስ 2
2
የእስራኤል ሕዝብ አምላኩን መተው
1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣
በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣
በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣
እንዴት እንደ ተከተልሽኝ አስታውሳለሁ።
3እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረች፤
የመከሩም በኵር ነበረች፤
የዋጧት ሁሉ በደለኞች ሆኑ፤
መዓትም ደረሰባቸው’ ”
ይላል እግዚአብሔር።
4የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ወገን ሁላችሁ፣
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣
ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣
ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣
ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው?
6እነርሱም፣ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፣
በወና ምድረ በዳ፣
በጐድጓዳና በበረሓ መሬት፣
በደረቅና በጨለማ#2፥6 ወይም በሞት ጥላ ቦታ፣
ሰው በማያልፍበትና በማይኖርበት ስፍራ
የመራን እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው አልጠየቁም።
7እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣
ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤
እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤
ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።
8‘እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው
ካህናቱ አልጠየቁም፤
ከሕጉ ጋራ የሚውሉት አላወቁኝም፤
መሪዎቹ ዐመፁብኝ፤
ነቢያቱም በበኣል ስም ተነበዩ፤
ከንቱ ነገሮችን ተከተሉ።
9“ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤
ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።”
ይላል እግዚአብሔር።
10“ወደ ኪቲም#2፥10 ኪቲም ቆጵሮስና የምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ ማለት ነው። ጠረፍ ተሻገሩና እዩ፤
ወደ ቄዳርም#2፥10 ቄዳር በሶርያዊ ዓረቢያ ምድረ በዳ የሚገኙ የበዶይን ነገዶች መኖሪያ፤ ልካችሁ በጥንቃቄ መርምሩ፣
እንዲህ ዐይነት ነገር ተደርጎ ያውቅ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤
11የእውነት አማልክት ባይሆኑም እንኳ፣
አማልክቱን የለወጠ ሕዝብ አለን?
ሕዝቤ ግን ክብራቸው#2፥11 የዕብራውያን የጥንት ጸሐፍት ትውፊት የሆነው የማሶሬቲክ ጽሑፍ ክብሬን ይላል። የሆነውን፣
በከንቱ ነገር ለወጡ።
12ሰማያት ሆይ፤ በዚህ ተገረሙ፤
በታላቅ ድንጋጤም ተንቀጥቀጡ፤”
ይላል እግዚአብሔር።
13“ሕዝቤ ሁለት ኀጢአት ፈጽመዋል፤
ሕያው የውሃ ምንጭ የሆንሁትን፣
እኔን ትተዋል፤
ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓዶች፣
ለራሳቸው ቈፍረዋል።
14እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውልድ ባሪያ?
ታዲያ፣ ስለ ምን ለብዝበዛ ተዳረገ?
15አንበሶች በርሱ ላይ አገሡ፤
በኀይለኛ ድምፅም ጮኹበት።
ምድሩን ባድማ አድርገውበታል፤
ከተሞቹ ተቃጥለዋል፤ ወናም ሆነዋል።
16ደግሞም የሜምፊስና#2፥16 ሜምፎስ በዕብራይስጡ ኖፍ ይላል፤ ወይም ጭንቅላትሽን ፈጠፈጡ ወይም ሰነጠቀ የጣፍናስ ሰዎች፣
መኻል ዐናትሽን ላጩሽ።
17በመንገድ የሚመራሽን፣
እግዚአብሔር አምላክሽን በመተውሽ፣
ይህን በራስሽ ላይ አላመጣሽምን?
18ከሺሖር#2፥18 የአባይ ወንዝ አንዱ ተነጣይ ጅረት ነው። ወንዝ ውሃ ለመጠጣት፣
አሁንስ ለምን ወደ ግብጽ ወረድሽ?
ከኤፍራጥስ ወንዝስ ውሃ ለመጠጣት፣
ወደ አሦር መውረድ ለምን አስፈለገሽ?
19ክፋትሽ ቅጣት ያስከትልብሻል፤
ክሕደትሽም ተግሣጽ ያመጣብሻል፤
እግዚአብሔር አምላክሽን ስትተዪ፣
እኔንም መፍራት ችላ ስትይ፣
ምን ያህል ክፉና መራራ እንደሚሆንብሽ
አስቢ፤ እስኪ አስተውዪ፤”
ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
20“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰበርሁ፤
እስራትሽን በጣጠስሁ፤
አንቺም፣ ‘አላገለግልህም’ አልሽ፤
ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ሥር፣
በእያንዳንዱም ለምለም ዛፍ ሥር፣
ለማመንዘር ተጋደምሽ።
21እኔ፣ እንደ ምርጥ የወይን ተክል፣
ጤናማና አስተማማኝ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤
ታዲያ ብልሹ የዱር ወይን ተክል ሆነሽ፣
እንዴት ተለወጥሽብኝ?
22በልዩ ቅጠል ብትታጠቢ፣
ብዙ ሳሙና ብትጠቀሚም፣
የበደልሽ ዕድፍ አሁንም በፊቴ ነው፤”
ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
23“ ‘አልረከስሁም፣
በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ?
በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽ
እስኪ አስቢ፣
ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤
እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤
24በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣
በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤
ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል?
ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም
በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች።
25እግርሽ እስኪነቃ አትሩጪ፤
ጕረሮሽም በውሃ ጥም እስኪደርቅ አትቅበዝበዢ።
አንቺ ግን፣ ‘በከንቱ አትድከም፤
ባዕዳን አማልክትን ወድጃለሁ፤
እነርሱን እከተላለሁ’ አልሽ።
26“ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፣
የእስራኤልም ቤት ዐፍሯል፤
እነርሱ፣ ንጉሦቻቸውና ሹሞቻቸው፣
ካህናታቸውና ነቢያታቸው እንዲሁ ያፍራሉ።
27ዛፉን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ’
ድንጋዩንም፣ ‘አንተ ወለድኸኝ’ አሉ፤
ፊታቸውን ሳይሆን፣
ጀርባቸውን ሰጥተውኛልና፤
በመከራቸው ጊዜ ግን፣
‘መጥተህ አድነን’ ይላሉ።
28ታዲያ፣ ልታመልካቸው ያበጀሃቸው አማልክት ወዴት ናቸው?
በመከራህ ጊዜ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ፣
ይሁዳ ሆይ፤ እስኪ ይምጡና ያድኑህ፤
የከተሞችህን ቍጥር ያህል፣
የአማልክትህም ብዛት እንዲሁ ነውና።
29“ለምን በእኔ ታማርራላችሁ?
ያመፃችሁብኝ እናንተ ሁላችሁ ናችሁ፤”
ይላል እግዚአብሔር።
30“ልጆቻችሁን በከንቱ ቀጣኋቸው፤
እነርሱም አልታረሙም።
ሰይፋችሁ እንደ ተራበ አንበሳ
ነቢያታችሁን በልቷል።
31“የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤
“እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣
ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን?
ሕዝቤ፣ ‘እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤
ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?
32ለመሆኑ ቈንጆ ጌጣጌጧን፣
ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን?
ሕዝቤ ግን፣
እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል።
33ፍቅርን ለመፈለግ እንዴት ሥልጡን ነሽ?
ልክስክስ ክፉ ሴቶች እንኳ ከመንገድሽ ብዙ ክፋት ይማራሉ።
34በስርቆት ያልያዝሻቸው፣
የንጹሓን ድኾች ደም፣
በልብስሽ ላይ ተገኝቷል።
ይህን ሁሉ አድርገሽም፣
35‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤
በርግጥ ቍጣው ከእኔ ርቋል’ ትያለሽ።
እኔ ግን እፈርድብሻለሁ፤
‘ኀጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና።
36መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣
ለምን ትሮጫለሽ?
አሦር እንዳዋረደሽ፣
ግብጽም እንዲሁ ያዋርድሻል።
37የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣
በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣
እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ
ከዚያም ትወጫለሽ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.