ኤርምያስ 30
30
የእስራኤል ሕዝብ መመለስ
1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ 2“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው። 3እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቧል፤#30፥3 ወይም የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ዕድል ፈንታ እመልሳለሁ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”
4 እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ 5“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቷል፤
ሰላምም የለም።
6እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤
ወንድ መውለድ ይችላል?
ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣
እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣
የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?
7ወዮ ለዚያ ቀን!
እንደዚያም ያለ አይኖርም፤
ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤
ነገር ግን ይተርፋል።
8“ ‘በዚያ ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤
‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤
እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤
ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዟቸውም።
9ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣
ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣
ለዳዊት ይገዛሉ።
10“ ‘ስለዚህ፤ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤
እስራኤል ሆይ፤ አትደንግጥ፤’
ይላል እግዚአብሔር።
‘አንተን ከሩቅ አገር፣
ዘርህንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ፤
ያዕቆብ ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፤
የሚያስፈራውም አይኖርም።
11እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አድንሃለሁም’
ይላል እግዚአብሔር፤
‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤
እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤
አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤
በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣
ያለ ቅጣት አልተውህም።’
12“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘ስብራትህ የማይጠገን፣
ቍስልህም የማይድን ነው።
13የሚሟገትልህ ሰው የለም፤
ለቍስልህ መድኀኒት አይኖርም፤
ፈውስም አታገኝም።
14ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤
ስለ አንተም ግድ የላቸውም።
ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤
እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤
በደልህ ታላቅ፣
ኀጢአትህም ብዙ ነውና።
15ፈውስ ለማይገኝለት ሕመምህ፣
ስለ ቍስልህ ለምን ትጮኻለህ?
በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ስለ ሆነ፣
እነዚህን ሁሉ አድርጌብሃለሁና።
16“ ‘ነገር ግን አሟጥጠው የበሉህ ሁሉ እንደዚያው ይበላሉ፤
ጠላቶችህ ሁሉ ለምርኮ ዐልፈው ይሰጣሉ፤
የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤
የሚበዘብዙህም ሁሉ ይበዘበዛሉ።
17አንተን ግን መልሼ ጤነኛ አደርግሃለሁ፤
ቍስልህንም እፈውሳለሁ፤’
ይላል እግዚአብሔር።
‘የተናቀች ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሃልና።
18“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤
ለማደሪያውም እራራለሁ፤
ከተማዪቱ በፍርስራሿ ጕብታ ላይ ትሠራለች፤
ቤተ መንግሥቱም በቀድሞ ቦታው ይቆማል።
19ከእነርሱም የምስጋና መዝሙር፣
የእልልታ ድምፅ ይሰማል።
እኔ አበዛቸዋለሁ፤
ቍጥራቸውም አይቀንስም፣
አከብራቸዋለሁ፤
የተናቁም አይሆኑም።
20ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤
ማኅበረ ሰቡም በፊቴ የጸና ይሆናል፤
የሚጨቍኗቸውን ሁሉ እቀጣለሁ።
21መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤
ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤
ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤
አለዚያማ ደፍሮ፣
ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?’ ይላል እግዚአብሔር።
22‘ስለዚህ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤
እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።’ ”
23እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማዕበል፣
በቍጣ ይነሣል፤
የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣
በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል።
24የልቡን ሐሳብ ሳይፈጽም፣
የእግዚአብሔር ቍጣ፣
እንዲሁ አይመለስም፤
በሚመጡትም ዘመናት፣
ይህን ታስተውላላችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
ኤርምያስ 30
30
የእስራኤል ሕዝብ መመለስ
1ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፤ 2“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፈው። 3እነሆ፣ ሕዝቤን እስራኤልንና ይሁዳን’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር የምመልስበት ጊዜ ተቃርቧል፤#30፥3 ወይም የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ዕድል ፈንታ እመልሳለሁ እነርሱም ይወርሷታል’ ይላል እግዚአብሔር።”
4 እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ 5“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቷል፤
ሰላምም የለም።
6እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤
ወንድ መውለድ ይችላል?
ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣
እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣
የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?
7ወዮ ለዚያ ቀን!
እንደዚያም ያለ አይኖርም፤
ለያዕቆብ የመከራ ጊዜ ነው፤
ነገር ግን ይተርፋል።
8“ ‘በዚያ ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤
‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤
እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤
ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዟቸውም።
9ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣
ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣
ለዳዊት ይገዛሉ።
10“ ‘ስለዚህ፤ አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤
እስራኤል ሆይ፤ አትደንግጥ፤’
ይላል እግዚአብሔር።
‘አንተን ከሩቅ አገር፣
ዘርህንም ከተማረኩበት ምድር እታደጋለሁ፤
ያዕቆብ ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፤
የሚያስፈራውም አይኖርም።
11እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አድንሃለሁም’
ይላል እግዚአብሔር፤
‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤
እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤
አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤
በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣
ያለ ቅጣት አልተውህም።’
12“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘ስብራትህ የማይጠገን፣
ቍስልህም የማይድን ነው።
13የሚሟገትልህ ሰው የለም፤
ለቍስልህ መድኀኒት አይኖርም፤
ፈውስም አታገኝም።
14ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤
ስለ አንተም ግድ የላቸውም።
ጠላት እንደሚመታ መታሁህ፤
እንደ ጨካኝም ቀጣሁህ፤
በደልህ ታላቅ፣
ኀጢአትህም ብዙ ነውና።
15ፈውስ ለማይገኝለት ሕመምህ፣
ስለ ቍስልህ ለምን ትጮኻለህ?
በደልህ ታላቅ፣ ኀጢአትህም ብዙ ስለ ሆነ፣
እነዚህን ሁሉ አድርጌብሃለሁና።
16“ ‘ነገር ግን አሟጥጠው የበሉህ ሁሉ እንደዚያው ይበላሉ፤
ጠላቶችህ ሁሉ ለምርኮ ዐልፈው ይሰጣሉ፤
የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤
የሚበዘብዙህም ሁሉ ይበዘበዛሉ።
17አንተን ግን መልሼ ጤነኛ አደርግሃለሁ፤
ቍስልህንም እፈውሳለሁ፤’
ይላል እግዚአብሔር።
‘የተናቀች ማንም የማይፈልጋት ጽዮን’ ብለውሃልና።
18“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ ‘እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤
ለማደሪያውም እራራለሁ፤
ከተማዪቱ በፍርስራሿ ጕብታ ላይ ትሠራለች፤
ቤተ መንግሥቱም በቀድሞ ቦታው ይቆማል።
19ከእነርሱም የምስጋና መዝሙር፣
የእልልታ ድምፅ ይሰማል።
እኔ አበዛቸዋለሁ፤
ቍጥራቸውም አይቀንስም፣
አከብራቸዋለሁ፤
የተናቁም አይሆኑም።
20ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤
ማኅበረ ሰቡም በፊቴ የጸና ይሆናል፤
የሚጨቍኗቸውን ሁሉ እቀጣለሁ።
21መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤
ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤
ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤
አለዚያማ ደፍሮ፣
ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?’ ይላል እግዚአብሔር።
22‘ስለዚህ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤
እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።’ ”
23እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማዕበል፣
በቍጣ ይነሣል፤
የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣
በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል።
24የልቡን ሐሳብ ሳይፈጽም፣
የእግዚአብሔር ቍጣ፣
እንዲሁ አይመለስም፤
በሚመጡትም ዘመናት፣
ይህን ታስተውላላችሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.