ዮሐንስ 13
13
ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ
1ጊዜው ልክ ከፋሲካ በዓል በፊት ነበረ፤ ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ። በዓለም የነበሩትን፣ የራሱ የሆኑትን ወደዳቸው፤ በፍጹም ፍቅሩም ወደዳቸው።#13፥1 ወይም እስከ መጨረሻው
2እራትም ቀርቦ ሳለ፣ ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ የስምዖንን ልጅ የአስቆሮቱን ይሁዳ ልብ አነሣሥቶ ነበር። 3ኢየሱስም፣ አብ ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር እንዳደረገለት፣ ከእግዚአብሔር እንደ ተላከና ወደ እግዚአብሔርም እንደሚመለስ ዐውቆ፣ 4ከእራት ተነሣ፤ መጐናጸፊያውን አስቀመጠ፤ ወገቡንም በፎጣ ታጠቀ። 5ከዚያም በመታጠቢያው ውሃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር እያጠበ በታጠቀው ፎጣ ያብስ ጀመር።
6ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ እግሬን ታጥባለህን?” አለው።
7ኢየሱስም መልሶ፣ “የማደርገውን አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።
8ጴጥሮስም፣ “የለም፤ እግሬን ከቶ አታጥብም” አለው።
ኢየሱስም፣ “ካላጠብሁህማ ከእኔ ጋራ ዕድል ፈንታ የለህም” አለው።
9ስምዖን ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ እንግዲያውስ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንም ራሴንም ዕጠበኝ” አለው።
10ኢየሱስም፣ “ገላውን የታጠበ ሰው የሚያስፈልገው እግሩን ብቻ መታጠብ ነው፤ የቀረው አካሉ ግን ንጹሕ ነው። ሁላችሁም ባትሆኑ፣ እናንተ ንጹሓን ናችሁ” አለው። 11“ሁላችሁም ንጹሓን አይደላችሁም” ያለው አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደ ሆነ ያውቅ ስለ ነበር ነው።
12እግራቸውን ዐጥቦ ካበቃ በኋላም፣ ልብሱን ለብሶ ተመልሶ በቦታው ተቀመጠ፤ እንዲህም አላቸው፤ “ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? 13እናንተ፣ ‘መምህርና፣ ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ ትክክል ነው፤ እንደምትሉኝ እንዲሁ ነኝና። 14እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ሆኜ ሳለሁ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተም እንደዚሁ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባችኋል። 15እኔ እንዳደረግሁላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ። 16እውነት እላችኋለሁ፤ ባሪያ ከጌታው፣ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። 17እንግዲህ እነዚህን ነገሮች ዐውቃችሁ ብትፈጽሙ ትባረካላችሁ።
ዐልፎ እንደሚሰጥ ኢየሱስ መናገሩ
18 “ስለ ሁላችሁ መናገሬ አይደለም፤ የመረጥኋቸውን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን፣ ‘እንጀራዬን የሚበላ ተረከዙን አነሣብኝ’ የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው። # 13፥18
መዝ 41፥9
19 “ሲፈጸም እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ፣ ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ነገርኋችሁ። 20እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የላክሁትን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔን የተቀበለም የላከኝን ይቀበላል።”
21ይህን ካለ በኋላም ኢየሱስ በመንፈሱ ታውኮ፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” ሲል መሰከረ።
22ደቀ መዛሙርቱም ማንን ማለቱ እንደ ሆነ ግራ ተጋብተው እርስ በርሳቸው ተያዩ። 23ከእነርሱ አንዱ፣ ኢየሱስ ይወድደው የነበረ ደቀ መዝሙር ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ ተቀምጦ ነበር። 24ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ደቀ መዝሙር በምልክት ጠቅሶ፣ “ማንን ማለቱ እንደ ሆነ ጠይቀው” አለው።
25እርሱም ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ፣ “ጌታ ሆይ፤ ማን ይሆን?” ብሎ ጠየቀው።
26ኢየሱስም፣ “ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው” አለው፤ ከዚያም ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለስምዖን ልጅ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው። 27ይሁዳም ቍራሹን እንጀራ እንደ ተቀበለ ወዲያው ሰይጣን ገባበት።
ኢየሱስም፣ “የምታደርገውን ቶሎ አድርግ” አለው፤ 28ይሁን እንጂ ኢየሱስ ለምን እንዲህ እንዳለው ማንም አላወቀም ነበረ። 29ይሁዳ ገንዘብ ያዥ ስለ ነበር፣ አንዳንዶቹ ለበዓሉ የሚያስፈልግ ነገር እንዲገዛ ወይም ለድኾች እንዲሰጥ ኢየሱስ የተናገረው መሰላቸው። 30ይሁዳም ያን ቍራሽ እንጀራ እንደ ተቀበለ ወጥቶ ሄደ፤ ሌሊትም ነበረ።
ጴጥሮስ እንደሚክደው ኢየሱስ መናገሩ
13፥37-38 ተጓ ምብ – ማቴ 26፥33-35፤ ማር 14፥29-31፤ ሉቃ 22፥33-34
31ይሁዳ ከወጣ በኋላ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ፤ በርሱም እግዚአብሔር ከበረ። 32እንግዲህ እግዚአብሔር በርሱ ከከበረ፣#13፥32 አያሌ የጥንት ቅጆች እግዚአብሔር በርሱ ከከበረ የሚለው ሐረግ የላቸውም። እግዚአብሔር ልጁን በራሱ ዘንድ ያከብረዋል፤ ወዲያውም ያከብረዋል።
33 “ልጆቼ ሆይ፤ ከእናንተ ጋራ የምቈየው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድ፣ ‘እኔ ወደምሄድበት ልትመጡ አትችሉም’ እንዳልኋቸው፣ አሁንም ለእናንተ ይህንኑ እላችኋለሁ።
34 “አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። 35እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።”
36ስምዖን ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ የምትሄደው ወዴት ነው?” አለው።
ኢየሱስም፣ “ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፤ ኋላ ግን ትከተለኛለህ” ሲል መለሰለት።
37ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ስለ አንተ ሕይወቴንም ቢሆን አሳልፌ እሰጣለሁ” አለው።
38ኢየሱስም፣ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕይወትህን በርግጥ ለእኔ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት እልሃለሁ፤ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ።
Currently Selected:
ዮሐንስ 13: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.