ዘሌዋውያን 21

21
ለካህናት የተሰጠ መመሪያ
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤ 2ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለ ሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣ 3እንዲሁም ባለማግባቷ ከርሱ ጋራ ስለምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል። 4ከርሱ ጋራ በጋብቻ ለሚዛመዱት#21፥4 ወይም እንደ መሪነቱ በሕዝቡ መካከል ራሱን አያርክስ። ግን ራሱን አያርክስ።
5“ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤ 6ለአምላካቸው የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።
7“ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ናቸውና። 8የአምላክህን ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁ#21፥8 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያችሁ እኔ እግዚአብሔር እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።
9“ ‘የካህን ሴት ልጅ ዝሙት ዐዳሪ ሆና ራሷን ብታረክስ፣ አባቷን ታዋርዳለች፤ በእሳት ትቃጠል።
10“ ‘ከወንድሞቹ መካከል ተለይቶ በራሱ ላይ ዘይት የፈሰሰበትና የክህነት ልብስ እንዲለብስ የተቀባው ካህን የራስ ጠጕሩን አይንጭ፤#21፥10 ወይም ጠጕሩን አይላጭ። ወይም ልብሱን አይቅደድ። 11አስከሬን ወዳለበት ስፍራ አይግባ፤ ስለ አባቱም ሆነ ስለ እናቱ ራሱን አያርክስ፤ 12የተቀደሰበት የአምላኩ የቅብዐት ዘይት በላዩ ስለ ሆነ የአምላኩን መቅደስ ትቶ በመሄድ መቅደሱን አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
13“ ‘ካህኑ የሚያገባት ሴት ድንግል ትሁን። 14ባል የሞተባትን፣ የተፋታችውን ወይም በዝሙት ዐዳሪነት የረከሰችውን ሴት አያግባ፤ ነገር ግን ከወገኖቹ መካከል ድንግሊቱን ያግባ። 15በወገኖቹ መካከል ዘሩን አያርክስ። እርሱን የምቀድሰው#21፥15 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለየው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”
16 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 17“አሮንን እንዲህ በለው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ከዘርህ እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው የአምላኩን ምግብ ይሠዋ ዘንድ አይቅረብ። 18ዕውር ወይም ዐንካሳ፣ የፊቱ ገጽታ ወይም የሰውነቱ ቅርጽ የተበላሸ ማንኛውም የአካል ጕድለት ያለበት ሰው አይቅረብ። 19እንዲሁም እግሩ ወይም እጁ ሽባ የሆነ፣ 20ጐባጣ ወይም ድንክ፣ ማንኛውም ዐይነት የዐይን እንከን ያለበት፣ የሚያዥ ቍስል ወይም እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ አይቅረብ። 21ከካህኑ ከአሮን ዘር ማንኛውም ዐይነት የአካል ጕድለት ያለበት ሰው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ሊያቀርብ አይምጣ፤ እንከን ያለበት ስለ ሆነ፣ የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። 22እርሱም የተቀደሰውንና እጅግ ቅዱስ የሆነውን የአምላኩን ምግብ ይብላ። 23ነገር ግን እንከን ያለበት ስለ ሆነ መቅደሴን እንዳያረክስ ወደ መጋረጃው አይቅረብ ወይም ወደ መሠዊያው አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው#21፥23 ወይም ቅዱስ አድርጌ የምለያቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”
24ሙሴም ይህን ለአሮን፣ ለልጆቹና ለእስራኤላውያን ሁሉ ነገራቸው።

Currently Selected:

ዘሌዋውያን 21: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ