ዘኍልቍ 10
10
የብር መለከቶች
1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ 2“ከተቀጠቀጠ ብር ሁለት መለከት አብጅ፤ ማኅበረ ሰቡን ለመጥሪያና ከሰፈራቸው እንዲነሡም ለመቀስቀሻ አድርጋቸው። 3ሁለቱ መለከቶች ሲነፉ ማኅበረ ሰቡ በሙሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አንተ ዘንድ ይሰብሰብ፤ 4ነገር ግን አንዱ መለከት ብቻ ከተነፋ አለቆች ማለት የእስራኤል ጐሣ መሪዎች አንተ ዘንድ ይሰብሰቡ፤ 5መለከቱ ከፍ ባለ ድምፅ ሲነፋ በስተምሥራቅ የሰፈሩት ነገዶች ጕዞ ይጀምሩ፤ 6መለከቱ ከፍ ባለ ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ሲነፋ በስተ ደቡብ የሰፈሩት ነገዶች ጕዞ ይጀምሩ፤ ከፍ ያለው ድምፅ ጕዞ ለመጀመር ምልክት ይሆናል። 7ማኅበሩን ለመሰብሰብ መለከቶች ይነፉ፤ ነገር ግን ድምፁ አይጩኽ።
8“መለከቶቹን ካህናቱ የአሮን ልጆች ይንፉ፤ ይህም ለእናንተና ለሚመጡት ትውልድ የዘላለም ሥርዐት ይሁን። 9በገዛ ምድራችሁ በግፍ በመጣባችሁ ጠላት ላይ ስትዘምቱ መለከቶቹን ከፍ ባለ ድምፅ ንፉ፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትታሰባላችሁ፤ ከጠላታችሁም እጅ ትድናላችሁ። 10እንዲሁም በደስታችሁ ቀናት ማለት በተደነገጉት በዓሎቻችሁና የወር መባቻ በዓል ስታከብሩ በሚቃጠል መሥዋዕታችሁና በኅብረት መሥዋዕታችሁ#10፥10 በተለምዶ የድነት መሥዋዕት ማለት ነው። ላይ መለከቱን ንፉ፤ እነዚህም በአምላካችሁ ፊት መታሰቢያ ይሆኑላችኋል። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
እስራኤላውያን ከሲና ተነሡ
11በሁለተኛው ዓመት፣ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። 12ከዚያም እስራኤላውያን ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው ደመናው በፋራን ምድረ በዳ እስኪያርፍ ድረስ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ ተጓዙ። 13እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረትም ለመጀመሪያ ጊዜ ተጓዙ።
14በመጀመሪያ የይሁዳ ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር። 15የይሳኮር ነገድ ሰራዊት አለቃም የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበር። 16እንዲሁም የዛብሎን ነገድ ሰራዊት አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር። 17ከዚህ በኋላ ማደሪያው ተነቀለ፤ ድንኳኑን የተሸከሙት ጌርሶናውያንና ሜራሪያውያንም ጕዞ ጀመሩ።
18ቀጥሎም የሮቤል ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር። 19የስምዖን ነገድ ሰራዊት አለቃም የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ነበር። 20እንዲሁም የጋድ ነገድ ሰራዊት አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበር። 21ከዚህ በኋላ ቀዓታውያን ንዋያተ ቅድሳቱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ከመድረሳቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር።
22ቀጥሎም የኤፍሬም ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበር። 23እንዲሁም የምናሴ ነገድ ሰራዊት አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበር። 24የብንያም ነገድ ሰራዊት አለቃም የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበር።
25በመጨረሻም የዳን ሰፈር ሰራዊት ለሁሉም ክፍሎች የኋላ ደጀን በመሆን በዐርማቸው ሥር ተጓዙ፤ አለቃቸውም የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር። 26እንዲሁም የአሴር ነገድ ሰራዊት አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበር። 27እንዲሁም የንፍታሌም ነገድ ሰራዊት አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር። 28እንግዲህ የእስራኤል ሰራዊት የጕዞ አሰላለፍ ሥርዐት ይህ ነበር።
29በዚህ ጊዜ ሙሴ የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፣ “እነሆ፤ እግዚአብሔር፣ ‘እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ጕዞ ጀምረናል፤ በመልካም ሁኔታ ስለምናኖርህ ከእኛ ጋራ ሂድ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል በጎ ነገር ለማድረግ ቃል ገብቷልና አለው።”
30እርሱም መልሶ፣ “ይህስ አይሆንም፤ አልሄድም፤ ወደ አገሬና ወደ ወገኖቼ ተመልሼ እሄዳለሁ” አለው።
31ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እባክህ አትለየን፤ በምድር በዳ ውስጥ የት መስፈር እንደሚገባን አንተ ታውቃለህ፤ ዐይናችንም ትሆናለህ። 32ከእኛ ጋራ ብትሄድ እግዚአብሔር ከሚያደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እኛም እናደርግልሃለን።”
33ስለዚህ ከእግዚአብሔር ተራራ ተነሥተው የሦስት ቀን መንገድ ተጓዙ፤ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦትም በእነዚያ ሦስት ቀናት ውስጥ የሚያርፉበትን ቦታ በመፈለግ ፊት ፊታቸው ይሄድ ነበር። 34ከሰፈራቸው በሚነሡበት ጊዜ የእግዚአብሔር ደመና ቀን ቀን ከላያቸው ነበር።
35ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣
“እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ!
ጠላቶችህ ይበተኑ፤
የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ”
ይል ነበር።
36ባረፉ ጊዜም፣
“እግዚአብሔር ሆይ፤
በብዙ ሺሕ ወደሚቈጠሩት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር።
Currently Selected:
ዘኍልቍ 10: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.