የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍልቍ 12

12
ማርያምና አሮን ሙሴን ተቃወሙ
1ሙሴ ኢትዮጵያዊት ሴት አግብቶ ነበርና ባገባት ኢትዮጵያዊት ምክንያት ማርያምና አሮን ይነቅፉት ጀመር። 2እነርሱም፣ “ለመሆኑ እግዚአብሔር የተናገረው በሙሴ አማካይነት ብቻ ነውን? በእኛስ አልተናገረም?” ተባባሉ፤ እግዚአብሔርም ይህን ሰማ።
3ሙሴ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበር።
4ወዲያው እግዚአብሔር ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን፣ “ሦስታችሁም ውጡና ወደ መገናኛው ድንኳን ኑ” አላቸው፤ ሦስቱም ወጥተው ሄዱ። 5ከዚያም እግዚአብሔር በደመና ዐምድ ወረደ፤ በድንኳኑም ደጃፍ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፤ ሁለቱም ወደ እርሱ በቀረቡ ጊዜ፣ 6እንዲህ አላቸው፤ “ቃሌን ስሙ፤
“የእግዚአብሔር ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር፣
በራእይ እገለጥለታለሁ፤
በሕልምም እናገረዋለሁ።
7ለአገልጋዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤
እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።
8እኔ ከርሱ ጋራ የምነጋገረው ፊት ለፊት ነው፤
በግልጽ እንጂ በልዩ ዘይቤ አይደለም፤
እርሱ የእግዚአብሔርን መልክ ያያል።
ታዲያ እናንተ አገልጋዬን ሙሴን
ትቃወሙ ዘንድ ለምን አልፈራችሁም?”
9እግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እርሱም ትቷቸው ሄደ።
10ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ፣ እነሆ፤ ማርያም በለምጽ#12፥10 በዕብራይስጡ ትርጕም ለምጽ ብቻ ሳይሆን፣ የተለያዩ የቈዳ በሽታዎችንም ያመለክታል። ተመታች፤ እንደ በረዶም ነጣች። አሮንም ወደ እርሷ ዘወር ሲል ለምጽ ወርሷት አየ፤ 11ሙሴንም እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፤ በስንፍናችን የሠራነውን ኀጢአት እባክህ አትቍጠርብን። 12እርሷንም በእናቱ ማሕፀን ሳለ ሞቶ ግማሽ አካሉ ከተበላ በኋላ የተወለደ ጭንጋፍ መስላ እንድትቀር አታድርግ።”
13ስለዚህም ሙሴ፣ “አምላክ ሆይ፤ እባክህ ፈውሳት” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
14 እግዚአብሔርም ለሙሴ፣ “አባቷ እፊቷ ላይ ቢተፋባት እስከ ሰባት ቀን በኀፍረት መቈየት አይገባትምን? አሁንም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን እንድትገለል አድርግ፤ ከዚያ በኋላ ግን ልትመለስ ትችላለች” ሲል መለሰለት። 15ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተገለለች፤ ከዚያ እስክትመለስም ሕዝቡ ጕዞውን አልቀጠለም ነበር።
16ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ከሐጼሮት ተነሣ፤ በፋራን ምድረ በዳም ሰፈረ።

Currently Selected:

ዘኍልቍ 12: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ